Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 36:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 የእግዚአብሔርን ታላቅነት መርምረን ልንደርስበት አንችልም፤ የዘመኑንም ልክ መመርመር አይቻልም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 እነሆ፤ እግዚአብሔር ከአእምሯችን በላይ ታላቅ ነው! የዘመኑም ቍጥር ከመታወቅ ያልፋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 እነሆ፥ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ እኛም አናውቀውም። የዘመኑም ቍጥር አይመረመርም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 እነሆ፥ ኀያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነው፥ እኛም አና​ው​ቀ​ውም፤ የዘ​መ​ኑም ቍጥር አይ​መ​ረ​መ​ርም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 እነሆ፥ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ እኛም አናውቀውም። የዘመኑም ቍጥር አይመረመርም።

参见章节 复制




ኢዮብ 36:26
14 交叉引用  

“በውኑ እግዚአብሔር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ ሰማያት፥ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ሊይዝህ አይችልም፤ እኔ የሠራሁት ይህ ቤተ መቅደስማ ምንኛ ያንስ?


የአንተ ቀኖች እንደ ሰው ቀኖች ናቸውን ወይስ ያንተ ዕድሜ እንደ ሰው ዕድሜ አጭር ነውን?


እነዚህ ሁሉ እግዚአብሔር ከሚሠራቸው ነገሮች ጥቂቶቹ ናቸው፤ የምንሰማውም ሹክሹክታውን ብቻ ነው፤ የኀይሉን ነጐድጓድማ ማን ሊያስተውል ይችላል?”


የእግዚአብሔርን ሥራ የሰው ዘር ሁሉ አይቶታል፤ ሰዎች በሩቅ ይመለከቱታል።


“እግዚአብሔር ውሃን ከባሕር ወደ ላይ ይስባል፤ ከሰማይም ያዘንበዋል።


እግዚአብሔር ሊታይ አይቻልም፤ ሥልጣኑም ታላቅ ነው፤ እርሱም ትክክለኛ ፈራጅ ነው።


እግዚአብሔር አስደናቂ በሆነ ድምፁ ነጐድጓድን ያሰማል፤ እኛ ልንረዳው የማንችል ታላላቅ ነገሮችንም ያደርጋል።


እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ ከፍተኛ ምስጋናም የሚገባው ነው፤ ታላቅነቱም ሰው ከሚያስተውለው በላይ ነው።


ተራራዎችን ከመሥራትህና ዓለምንም ከመፍጠርህ በፊት፥ አንተ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም አምላክ ነህ።


አሁን በመስተዋት እንደምናየው ዐይነት በድንግዝግዝ እናያለን፤ በዚያን ጊዜ ግን በግልጥ እናያለን፤ አሁን የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያን ጊዜ ግን እግዚአብሔር እኔን የሚያውቀኝን ያኽል ሙሉ ዕውቀት ይኖረኛል።


እንደ መጐናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ፤ እነርሱም እንደ ልብስ ይለወጣሉ። አንተ ግን ሁልጊዜ ያው ነህ፤ ለዘመንህም ፍጻሜ የለውም” ይላል።


ወዳጆቼ ሆይ! እናንተ ግን በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመት እንደ አንድ ቀን መሆኑን ይህን አንድ ነገር አትርሱ።


跟着我们:

广告


广告