Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 36:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ሰዎች ሁልጊዜ በሚሠራው ሥራ በመዝሙር እንደሚያመሰግኑት። አንተም የእርሱን ሥራ በመዝሙር አመስግን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ሰዎች በመዝሙር ያወደሱትን፣ የርሱን ሥራ ማወደስ አትዘንጋ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ይልቁንም ሰዎች የዘመሩለትን ሥራውን ማክበርን አስታውስ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ሰዎች ሊሠ​ሩት ከሞ​ከ​ሩት በላይ፥ ሥራው ታላቅ እንደ ሆነ አስብ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ሰዎች የዘመሩትን ሥራውን ታከብር ዘንድ አስብ።

参见章节 复制




ኢዮብ 36:24
26 交叉引用  

ለእግዚአብሔር የምስጋና መዝሙር ዘምሩ፤ ያደረገውን አስደናቂ ነገር ሁሉ ተናገሩ፤


የእግዚአብሔርን ሥራ የሰው ዘር ሁሉ አይቶታል፤ ሰዎች በሩቅ ይመለከቱታል።


እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ብዙ ነገሮችን ፈጥረሃል፤ ሁሉንም በጥበብ አድርገሃል፤ ምድር አንተ በፈጠርካቸው ነገሮች ተሞልታለች።


ስላደረገላቸው ድንቅ ነገሮችና ስለ ዘለዓለማዊ ፍቅሩ የሰው ልጆች እግዚአብሔርን ያመስግኑ።


ለሰው ልጆች ስላደረገላቸው ድንቅ ነገሮችና ስለ ዘለዓለማዊ ፍቅሩ እግዚአብሔርን ያመስግኑ።


እነርሱም ለዘለዓለም የጸኑ ናቸው፤ የተሰጡትም በእውነትና በታማኝነት ነው።


ስላደረግኸው ድንቅ ነገር ሁሉና ስለ ታላቅ ክብርህ ይዘምሩልሃል።


እነርሱ ለእግዚአብሔር አድራጎትና ለእጁ ሥራ ትኲረት ስለማይሰጡ እርሱ ይሰባብራቸዋል፤ እንደገናም አይገነባቸውም።


የእግዚአብሔርን ታላቅነት ከእኔ ጋር አስታውቁ፤ በኅብረትም ስሙን እናክብር።


በመከራዬ ቀን መጠጊያዬና ምሽጌ ስለ ሆንክ ስለ ኀያልነትህ ክብርና ስለ ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ዘወትር በማለዳ እዘምራለሁ።


እርሱ ብቻ ተአምራትን የሚያደርገው፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!


ከዚህ በኋላ ሙሴና የእስራኤል ሕዝብ ከዚህ የሚከተለውን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ፦ “ፈረሱንና ፈረሰኛውን ወደ ባሕር በመጣል፥ ክብር የተሞላው ድል ስለ ተጐናጸፈ፥ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ።


እግዚአብሔር በኀይሉ ምድርን ሠራ፤ በጥበቡም ዓለምን ፈጠረ፤ በማስተዋሉም ሰማያትን ዘረጋ፤


“እግዚአብሔር የሚያሳየው ተአምር እንዴት ታላቅ ነው! እርሱ የሚፈጽመው ድንቅ ሥራ እንዴት ብርቱ ነው! እግዚአብሔር ለዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።


“እነሆ፥ እኔ ናቡከደነፆር ለሰማይ ንጉሥ ምስጋና፥ ክብርና ውዳሴ አቀርባለሁ፤ እርሱ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ነው፤ መንገዱም ፍትሓዊ ነው፤ በትዕቢት የሚመሩትንም ሁሉ ማዋረድ ይችላል።”


ማርያምም እንዲህ አለች፦ “ነፍሴ ጌታን ታመሰግናለች፤


በሰማይ ላይ የምታዩአቸውን ፀሐይንና ጨረቃን ወይም ከዋክብትን ወይም የሰማይን ሠራዊት ሁሉ በማምለክና ለእነርሱ በመስገድ እንዳትፈተኑ ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ እነዚህን ሁሉ ሌሎች ሕዝቦች ብቻ ያመልኩአቸው ዘንድ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋል።


የእግዚአብሔርን አገልጋይ የሙሴን መዝሙርና የበጉን መዝሙር እንዲህ እያሉ ይዘምሩ ነበር፥ “ሁሉን የምትችል ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና አስደናቂ ነው፤ የሕዝቦች ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነት ነው፤


በዚያን ቀን ዲቦራና የአቢኒዓም ልጅ ባራቅ ይህን መዝሙር ዘመሩ፦


跟着我们:

广告


广告