9 ‘እግዚአብሔርን ማስደሰት፥ ለሰው ምንም አይጠቅመውም’ ይላል።
9 ‘እግዚአብሔርን ለማስደሰት መሞከር፣ ለሰው አንዳች አይጠቅምም’ ብሏልና።
9 ሰው ከእግዚአብሔር ጕብኝት ሲኖረው እግዚአብሔር አይጐበኘውም አትበል።
እነዚያ ‘ክፉ ሰዎች መቅሠፍት በሚመጣበት ጊዜ ጒዳት አይደርስባቸውም፤ የእግዚአብሔር ቊጣም ሲገለጥ ያመልጣሉ’ ሲሉ ተናግረዋል።
እነርሱም ሁሉን የሚችለውን አምላክ፦ ‘ከእኛ ራቅ፤ ምን ልታደርግልን ትችላለህ?’ አሉት።
የአንተ መልካም ሥራ ሁሉን ለሚችል አምላክ ምን ይጠቅመዋል? የኑሮህስ ፍጹምነት ለእርሱ ምን ይረባዋል?
ሁሉን በሚችል አምላክ ይደሰታሉን? በየጊዜውስ የእግዚአብሔርን ስም ይጠራሉን?
‘ኃጢአት ባልሠራ ምን እጠቀማለሁ? ምንስ አተርፋለሁ?’ ብለህ ትጠይቅ ይሆናል።
በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፤ እርሱም የልብህን ፍላጎት ሁሉ ይሰጥሃል።
ሌባውን ስታይ ከእርሱ ጋር ትወዳጃለህ፤ ከአመንዝራዎችም ጋር በመስማማት ትተባበራለህ።
ሐሳቤን በቅንነት መጠበቄና በደልንም ከመሥራት መቈጠቤ ምን ጠቀመኝ?
ሕዝቡም “እነሆ እኛ እንጾማለን፤ አንተ ግን አትመለከተንም፤ የማትመለከተንስ ከሆነ ሰውነታችንን ለምን እናዋርዳለን?” ይላሉ። እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ “እነሆ እናንተ በምትጾሙበት ጊዜ የልባችሁን ፈቃድ ትፈጽማላችሁ፤ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ትጨቊናላችሁ፤
እናንተ ‘እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፤ ትእዛዞቹን መጠበቅና እንደ ሐዘንተኞች በሠራዊት አምላክ ፊት መመላለስ ምን ይጠቅመናል?