8 ጓደኞቹ ክፉ አድራጊዎች ናቸው፤ የሚውለውም ከክፉ አድራጊዎች ጋር ነው።
8 ከክፉ አድራጊዎች ጋራ ይተባበራል፤ ከኀጢአተኞችም ጋራ ግንባር ይፈጥራል።
8 ፈጽሞ ያልበደለ፥ ግፍን ከሚሠሩም ጋር ያልተባበረ፥ ከኃጥኣንም ጋር ያልሄደ፥ ማን ነው?
ኢዮብ ሆይ! ከንቱ ንግግርህ መልስ የማይሰጥበት ይመስልሃልን? ይህን ያኽልስ ስታፌዝ፥ የሚገሥጽህ የሌለ መሰለህን?
በደለኛነትህ በአነጋገርህ ይታወቃል፤ ነገር ግን በብልጠት አነጋገር ልትሸፍነው ትሞክራለህ።
ኢዮብም “እንዴት የሞኝ ሴት ንግግር ትናገሪያለሽ? እግዚአብሔር መልካም ነገር ሲሰጠን በደስታ እንቀበላለን፤ ታዲያ፥ መከራ ሲያመጣብን በእርሱ ላይ ማጒረምረም ይገባናልን?” አላት። ኢዮብ ምንም እንኳ ይህ ሁሉ መከራና ሥቃይ ቢደርስበት በእግዚአብሔር ላይ ክፉ ነገር በመናገር ኃጢአት አልሠራም።
“ኃጢአተኞች ይመላለሱበት የነበረው የዱሮውን መንገድ ትከተላለህን?
‘እግዚአብሔርን ማስደሰት፥ ለሰው ምንም አይጠቅመውም’ ይላል።
በክፉ ሰዎች ምክር የማይሄድ፥ የኃጢአተኞችን መንገድ የማይከተል፥ ከፌዘኞች ጋር ኅብረት የማያደርግ የተባረከ ነው።
ከአታላዮች ጋር አልወዳጅም፤ ከግብዞችም ጋር አልተባበርም፤
ሌባውን ስታይ ከእርሱ ጋር ትወዳጃለህ፤ ከአመንዝራዎችም ጋር በመስማማት ትተባበራለህ።
ልጄ ሆይ! እነዚህን ከመሰሉ ሰዎች ጋር አብረህ አትሂድ፤ ከእነርሱም ራቅ።
ከጥበበኞች የሚወዳጅ ጥበበኛ ይሆናል። ማስተዋል ከጐደላቸው ሰዎች ጋር ጓደኛ የሚሆን ግን ይጐዳል።
ጥበብ ከክፉ ሰዎች መንገድና ከጠማማ ንግግራቸው ያድንሃል።
ክፉ ሰዎች በሚሄዱበት መንገድ አትሂድ፤ ምሳሌነታቸውንም አትከተል።
አትታለሉ፤ “መጥፎ ጓደኛ ጥሩውን ጠባይ ያበላሻል።”