Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 34:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ታዲያ፥ አንተ ንስሓ መግባት እንቢ እያልክ፥ አንተ በምታቀርበው ሐሳብ መሠረት እግዚአብሔር ምኞትህን እንዲፈጽምልህ ትፈልጋለህን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ታዲያ አንተ ለመናዘዝ ፈቃደኛ ሳትሆን፤ እግዚአብሔር እንደ ወደድህ ይከፍልሃልን? መወሰን ያለብህ አንተ ነህ እንጂ፣ እኔ አይደለሁም፤ እንግዲህ የምታውቀውን ንገረኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 በውኑ አንተ ተቃውመኸዋልና ሽልማቱ አንተ እንደምትወድደው ይሆናልን? እኔ ሳልሆን አንተ ነህ የምትመርጠው፥ ስለዚህ የምታውቀውን ተናገር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 በውኑ አንተ ከእኔ ትርቅ ዘንድ፥ እኔ ከአ​ንተ የተ​ቀ​በ​ል​ሁት አለን? አንተ ትመ​ር​ጣ​ለህ እንጂ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምና፤ ስለ​ዚህ የም​ታ​ው​ቀው ካለ ተና​ገር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 በውኑ አንተ ጥለኸዋልና ፍዳው አንተ እንደምትወድደው ይሆናልን? አንተ ትመርጣለህ እንጂ እኔ አይደለሁም፥ ስለዚህ የምታውቀውን ተናገር።

参见章节 复制




ኢዮብ 34:33
20 交叉引用  

በከንቱ ነገር እየተማመነ ራሱን አያታል፤ በዚህም ዋጋ ቢስ ሆኖ ይቀራል።


አንተ ብትቈጣ ራስህን ትጐዳለህ እንጂ በአንተ ቊጣ ምድር ባዶ አትሆንም። አለቶችም ከስፍራቸው አይነቃነቁም።


የምትለው ነገር ካለህ መልስልኝ፤ እኔ አንተን ነጻ ለማውጣት ስለምፈልግ ተናገር።


“የምትችል ከሆነ ለንግግሬ መልስ ስጠኝ፤ ክርክሮችህን አመቻችተህ ቆመህ ተከራከረኝ።


እግዚአብሔር ለሰው እንደ ሥራው ይከፍለዋል፤ በአካሄዱም መጠን የሚገባውን ያደርግለታል።


“የሚሰሙኝ ሰዎች እንዲህ ይሉኛል፤ የሚያስተውሉ ሰዎች እንዲህ ይላሉ፦


ከሰማይ በታች ያለው ነገር ሁሉ የእኔ ነው፤ ታዲያ፥ እንድመልስለት ለእኔ ያበደረ ማነው?


የፈለገውን ቢወስድ ማንም አይከለክለውም፤ ‘ለምን እንዲህ ታደርጋለህ?’ ብሎ ሊጠይቀው የሚደፍርም የለም።


በሰማይና በምድር፥ በጥልቅ ባሕሮችም የወደደውን ሁሉ ያደርጋል።


ይህን ስታደርግ ዝም በማለቴ እኔም እንደ አንተ የሆንኩ መሰለህን? አሁን ግን ፊት ለፊት ነገሩን ገልጬ እገሥጽሃለሁ።


ደጋግ ሰዎች በምድር ላይ ሳሉ የመልካም ሥራቸውን ዋጋ ያገኛሉ፤ ክፉዎችና ኃጢአተኞች ግን እጅግ የበረታ ቅጣትን ይቀበላሉ።


ከሠሪው ጋር ለሚከራከር ወዮለት! እርሱ እኮ ከሸክላ ዕቃዎች እንደ አንዱ ነው፤ አንድ የሸክላ ሥራ ሸክላ ሠሪውን “ምንድን ነው የምታደርገው? እጀታውስ የት አለ?” ብሎ ሊጠይቅ ይችላልን?


ጽዋውን ከእጅህ ተቀብለው ለመጠጣት እምቢ የሚሉ ከሆነ፥ ‘ከዚህ ጽዋ መጠጣት እንዳለባችሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አዞአል’ ብለህ ንገራቸው።


ለእግዚአብሔር የሚያበድርና ያበደረውንም የሚወስድ ማነው?”


አንተ ሰው! ከእግዚአብሔር ጋር ለመከራከር ምን መብት አለህ? የሸክላ ዕቃ ሠሪውን “ለምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ?” ሊለው ይችላልን?


ወደፊትም የሚቀበለውን ዋጋ ስለ ተመለከተ ከግብጽ ሀብት ይልቅ ስለ መሲሑ መዋረድ የበለጠ መሆኑን አሰበ።


በመላእክት አማካይነት የተነገረው ቃል እርግጠኛ ሆኖአል፤ ይህንንም ቃል የሚተላለፍና ለዚህም ቃል የማይታዘዝ ተገቢውን ቅጣት ይቀበላል፤


跟着我们:

广告


广告