Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 34:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ድኾችን በመጨቈን ወደ እግዚአብሔር እንዲጮኹ አድርገዋቸዋል፤ እግዚአብሔርም የድኾችን ጩኸት ሰምቶአል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 የድኾች ልቅሶ ወደ እርሱ እንዲደርስ ሰበብ ሆኑ፤ የመከረኞችን ጩኸት ሰማ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 እር​ሱም የድ​ሆ​ችን ጩኸት በእ​ነ​ርሱ ላይ ይመ​ል​ሳል፥ የች​ግ​ረ​ኞ​ች​ንም ልቅሶ ይሰ​ማል።

参见章节 复制




ኢዮብ 34:28
21 交叉引用  

ወደ እርሱም በምትጸልይበት ጊዜ የለመንከውን ሁሉ ስለሚፈጽምልህ፥ ስለትህን ትከፍላለህ።


በየከተማው ለመሞት የሚያጣጥሩ ሰዎች ይቃትታሉ፤ የቈሰሉትም ሰዎች ርዳታ በመጠየቅ ይጮኻሉ። እግዚአብሔር ግን በእነርሱ ላይ የተሠራውን ግፍ አልተመለከተም።


በዚያን ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል፤ ጸሎቱንም እግዚአብሔር ይሰማዋል የእግዚአብሔርን ፊት አይቶ ይደሰታል፤ እግዚአብሔርም ስለጽድቁ ዋጋውን ይከፍለዋል።


“እግዚአብሔርን የሚክድና ሕዝቡን የሚያጠምድ ንጉሥ ሲነግሥ፥ እግዚአብሔር ዝም ቢል፥ ወይም ፊቱን ቢሰውር ማን ሊወቅሰው ይችላል?


ሰዎች ጭቈና ሲበዛባቸው ይጮኻሉ፤ ከሚበረታባቸውም እጅ የሚታደጋቸውን ለማግኘት፥ አቤቱታ ያሰማሉ።


ድኾችን ከጠላቶቻቸው ሰይፍ ያድናቸዋል፤ ችግረኞችንም ከጨቋኞች እጅ ነጻ ያወጣቸዋል።


ቀጥተኛና ንጹሕ ከሆንክ፥ እርሱ ፈጥኖ ወደ ተገቢ ቦታህ ይመልስሃል።


እግዚአብሔር ግን “ችግረኞች ተጨቊነዋል፤ ስደተኞች በመከራ ብዛት ይቃትታሉ፤ ስለዚህ እነርሱ የሚፈልጉትን ደኅንነት ለመስጠት እነሣለሁ” ይላል።


እግዚአብሔር ሆይ! ልመናዬን ወደ አንተ አቅርቤ መልስህን ስጠብቅ በየማለዳው ጸሎቴን ስማ።


ባልዋ የሞተባትን መበለት ወይም አባትና እናት የሞቱበትን ድኻ ዐደግ አታጒላሉ።


ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “በግብጽ ያለውን የሕዝቤን ጭንቀት አይቻለሁ፤ በአስጨናቂዎቻቸው ምክንያት የሚጮኹትን ጩኸት ሰምቼአለሁ፤ ጭንቀታቸውንም ዐውቃለሁ።


እነሆ፥ የሕዝቤ የእስራኤል ጩኸት ወደ እኔ ደርሶአል፤ ግብጻውያን በእነርሱ ላይ የሚያደርሱባቸውን የግፍ ጭቈና ተመልክቻለሁ፤


ይህም የሠራዊት አምላክ የወይን ቦታ የተባለው የእስራኤል ሕዝብ ነው፤ እርሱም የይሁዳ ሕዝብ ደስ የሚሰኝበት ተክል ነው። መልካም ሥራ እንዲሠሩ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ በዚህ ፈንታ ነፍሰ ገዳዮች ሆኑ፤ ቅን ፍርድ ይሰጣሉ ብሎ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ እነርሱ ግን ፍርድን በማጓደላቸው የሕዝቡ ጩኸት በዛ።


ጆሮህን ወደ እኔ መልስ፤ ለእርዳታም ድረስልኝ” የሚለውን ልመናዬን ሰምተሃል፤ ስለዚህ ዕረፍትን ስጠኝ።


የዕዳ መሰረዣ ሰባተኛ ዓመት ደርሶአል በማለት ችግረኛ ወገንህን ብድር አትከልክለው፤ እንዲህ ያለ ክፉ ሐሳብም ወደ ልብህ አይግባ፤ ብድር መስጠትን ብትከለክል ችግረኛው ወገንህ ወደ እግዚአብሔር ይጮኻል፤ ስለዚህ በአንተ ላይ እንደ በደል ይቈጠርብሃል።


ይሁን እንጂ በእርሻችሁ ሲያጭዱ ለዋሉት ሠራተኞች ዋጋቸውን ስላልከፈላችሁ እነሆ፥ የተቃውሞ ጩኸታቸው ይሰማል፤ የመከር ሰብሳቢዎቹንም ጩኸት የሠራዊት ጌታ ሰምቶአል።


跟着我们:

广告


广告