Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 33:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እነሆ፥ እኔና አንተ በእግዚአብሔር ፊት እኩል ነን፤ እኔም የተፈጠርኩት ከጭቃ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በእግዚአብሔር ፊት እኔም እንደ አንተው ነኝ፤ የተፈጠርሁትም ደግሞ ከዐፈር ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እነሆ፥ በእግዚአብሔር ፊት እኔ እንደ አንተ ነኝ፥ እኔም እንዳንተ ከጭቃ የተቀረጽሁ ነኝ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 አንተ እንደ እኔ ከጭቃ የተ​ፈ​ጠ​ርህ ነህ፥ የሁ​ላ​ች​ንም ተፈ​ጥሮ ከዚ​ያው ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እነሆ፥ በእግዚአብሔር ፊት እኔ እንደ አንተ ነኝ፥ እኔ ደግሞ ከጭቃ የተፈጠርሁ ነኝ።

参见章节 复制




ኢዮብ 33:6
15 交叉引用  

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ከመሬት ዐፈር ወስዶ፥ ሰውን ከዐፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም ሕይወትን የሚሰጥ እስትንፋስ “እፍ” አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ፍጡር ሆነ።


ወደ መጣህበት ወደ መሬት እስክትመለስ ድረስ፥ እንጀራህን በግንባርህ ላብ ትበላለህ።” ዐፈር ነህና፥ ወደ ዐፈርም ትመለሳለህ።


ያዕቆብም ራሔልን ተቈጥቶ “ልጅ ልሰጥሽና ልከለክልሽ የምችል እግዚአብሔር መሰልኩሽን?” አላት።


እንደ ሸክላ ዕቃ ከዐፈር እንደ ሠራኸኝ አስብ፤ ታዲያ፥ አሁን መልሰህ እንደ ትቢያ ልታደቀኝ ነውን?


ምሳሌያዊ አነጋገራችሁ እንደ ዐመድ ዋጋ ቢሶች ናቸው፤ ክርክራችሁም እንደ ሸክላ ተሰባብሮ ይወድቃል።


ነገር ግን የእኔ ንግግር ከኀያሉ እግዚአብሔር ጋር ነው፤ ከእርሱ ጋርም እከራከራለሁ።


ምንም እንኳ ሀብታም ቢሆን ብስጭት ይደርስበታል፤ ብዙ ችግርም ያጋጥመዋል።


“ምነው የሚሰማኝ ባገኘሁ! መከላከያዬን አቀርባለሁ፤ ሁሉን ቻይ አምላክ ይመልስልኝ! ምነው ከሳሼም የክሱን ዝርዝር በጽሑፍ አቅርቦልኝ ባየሁት!


ታዲያ፥ ምስጥ ሳይበላቸው የሚፈርሱ መሠረታቸው ዐፈር በሆነና ከሸክላ በተሠራ ቤት ውስጥ በሚኖሩትማ ላይ እንዴት ይተማመንባቸዋል?


እርሱ አንተን ወክሎ ይናገራል፤ በአንተም ስም ቃሉን ለሕዝቡ ያስተላልፋል፤ አንተም ለእርሱ እንደ አምላክ ትሆናለህ።


ነገር ግን ይህ ከሁሉ የሚበልጠው ኀይል የእግዚአብሔር እንጂ የእኛ አለመሆኑ እንዲታወቅ ይህን ክቡር ነገር እንደ ሸክላ ዕቃ ሆነን ይዘነዋል።


ይህ እንደ ድንኳን ጊዜያዊ የሆነው ምድራዊው ሥጋችን ሲፈርስ በሰው እጅ ሳይሆን በእግዚአብሔር የታነጸ ዘለዓለማዊ መኖሪያ በሰማይ እንዳለን እናውቃለን።


እግዚአብሔር ሰዎችን በእኛ አማካይነት ስለሚጠራ እኛ የክርስቶስ እንደራሴዎች ነን፤ ስለዚህ “ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ!” ብለን በክርስቶስ ስም እንለምናችኋለን።


跟着我们:

广告


广告