Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 33:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 በዚህ ዐይነት ሰዎች ኃጢአት ከመሥራት እንዲቈጠቡ ያደርጋል፤ ትዕቢትንም ከእነርሱ ያስወግዳል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ሰውን ከክፉ ሥራው ይመልሳል፤ ከትዕቢት ይጠብቃል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ሰውን ከክፉ ሥራው ይመልሰው ዘንድ፥ ሰውንም ከትዕቢት ይቆጥበው ዘንድ፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ሰውን ከኀ​ጢ​አቱ ይመ​ል​ሰው ዘንድ፥ ሥጋ​ው​ንም ከው​ድ​ቀት ያድ​ነው ዘንድ፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ሰውን ከክፉ ሥራው ይመልሰው ዘንድ፥ ከሰውም ትዕቢትን ይሰውር ዘንድ፥

参见章节 复制




ኢዮብ 33:17
16 交叉引用  

ነገር ግን አንድ ሌሊት እግዚአብሔር በሕልም ተገልጦ አቤሜሌክን “ይህች ሴት ባለባል ስለ ሆነች እርስዋን በመውሰድህ ምክንያት ትሞታለህ” አለው።


እግዚአብሔርም በሕልም እንዲህ አለው፦ “በንጹሕ ኅሊና እንዳደረግህ ዐውቄአለሁ፤ ወደ እርስዋ ቀርበህ በእኔ ፊት ኃጢአት እንዳትሠራ ያደረግኩህም ስለዚህ ነው።


ሕዝቅያስ ግን ልቡ በትዕቢት ተሞልቶ ስለ ነበር፥ እግዚአብሔር ስላደረገለት ቸርነት ሁሉ ተገቢ ምስጋና አላቀረበም፤ ከዚህም የተነሣ በእርሱ፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ሕዝብ ብርቱ ሥቃይ ደረሰባቸው።


“የዕድሜዬ ዘመን ተፈጽሞአል፤ ዕቅዴና የልቤ ምኞት ከንቱ ሆኖ ቀርቶአል።


በዚያም ጊዜ ሰዎች ቃሉን እንዲሰሙ ያደርጋል፤ በሚሰጣቸውም ማስጠንቀቂያ ያስደነግጣቸዋል።


ሕይወታቸውንም ከጥፋት ይጠብቃል፤ ከሞት መቅሠፍትም ይታደጋቸዋል።


ሕይወት አስቸጋሪ ቢሆንም ለሁሉም ነገር ጊዜና ቦታ አለው።


ትዕቢተኞች ይዋረዳሉ፤ ኩራተኞችም ይቀላሉ፤ እግዚአብሔር ብቻ በክብር ከፍ ከፍ ይላል፤


ይህንማ ያቀደው የሠራዊት አምላክ ነው፤ እርሱም ይህን ያቀደው ባደረጉት ነገር መታበያቸውን እንዲተዉ ለማድረግና የተከበሩትንም ሰዎች ለማዋረድ ብሎ ነው።


ስለዚህ መንገድዋን በእሾኽ እዘጋዋለሁ፤ መውጫ በር እንዳታገኝም ዙሪያውን በግንብ አጥራለሁ።


ከዚህም በላይ ጲላጦስ በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ፦ “በእርሱ ምክንያት ዛሬ ሌሊት በሕልም ብዙ ተሠቃይቻለሁና በዚያ በንጹሕ ሰው ላይ ምንም እንዳታደርግ” ስትል ላከችበት።


ከነዚህ ከተገለጡልኝ ታላላቅ ነገሮች የተነሣ እንዳልታበይ ሥጋዬን እንደ እሾኽ የሚወጋ ሥቃይ ተሰጠኝ፤ ይህም የሰይጣን መልእክተኛ በመሆን እየጐሸመ በማሠቃየት እንዳልታበይ ያደርገኛል።


ሊያዋርድህና ሊፈትንህ፥ በመጨረሻም መልካም ነገር ሊያደርግልህ የቀድሞ አባቶችህ ተመግበው የማያውቁትን መና በምድረ በዳ ሰጠህ።


በጌታ ፊት ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤ እርሱም ከፍ ያደርጋችኋል።


跟着我们:

广告


广告