Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 33:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በሌሊት ሰዎች በአልጋ ላይ ተኝተው አፍላ እንቅልፍ ይዞአቸው ሳለ፥ እግዚአብሔር በሕልምና በራእይ ይናገራል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሰዎች ዐልጋቸው ላይ ተኝተው ሳሉ፣ ከባድ እንቅልፍ ሲወድቅባቸው፣ በሕልም፣ በሌሊትም ራእይ ይናገራል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በሕልም፥ በሌሊት ራእይ፥ አፍላ እንቅልፍ በሰዎች ላይ ሲወድቅ፥ በአልጋ ላይ ተኝተው ሳሉ፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በአ​ልጋ ላይ ተኝ​ተው ሳሉ፥ በሰ​ዎች ላይ ታላቅ ድን​ጋ​ጤን ያመ​ጣል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በሕልም፥ በሌሊት ራእይ፥ አፍላ እንቅልፍ በሰዎች ላይ ሲወድቅ፥ በአልጋ ላይ ተኝተው ሳሉ፥

参见章节 复制




ኢዮብ 33:15
15 交叉引用  

የፀሐይ መጥለቂያ ሰዓት እየተቃረበ ሲሄድ አብራምን ከባድ እንቅልፍ ያዘው፤ እነሆ፥ ድንጋጤና ታላቅ ጨለማ መጣበት።


ነገር ግን አንድ ሌሊት እግዚአብሔር በሕልም ተገልጦ አቤሜሌክን “ይህች ሴት ባለባል ስለ ሆነች እርስዋን በመውሰድህ ምክንያት ትሞታለህ” አለው።


በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ለላባ በሕልም ተገለጠለትና “ያዕቆብን፥ ክፉም ሆነ ደግ እንዳትናገረው ተጠንቀቅ” አለው።


እግዚአብሔር፥ ሌሊት በራእይ ተገለጠለትና “ያዕቆብ! ያዕቆብ!” ብሎ ጠራው። እርሱም “አቤት ጌታ ሆይ፥ እነሆ አለሁ” አለ።


“ከዕለታት አንድ ቀን ምሥጢራዊ መልእክት ወደ እኔ መጣ፤ ይህንንም መልእክት በሹክሹክታ ሰማሁት።


ሰዎች ከባድ እንቅልፍ በሚይዛቸውና በሚያስጨንቅ የሌሊት ቅዠት ጊዜ፥


ሕልም ያለመ ነቢይ ቢኖር ሕልሙን ብቻ ይናገር፤ ቃሌን የሰማ ነቢይ ግን ያንኑ ቃል በታማኝነት ይናገር፤ ገለባ ከስንዴ ጋር ምን ግንኙነት አለው?


ናቡከደነፆር በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ሕልም አየ፤ በጣምም ስለ ተጨነቀ እንቅልፍ አጣ።


በዚያኑ ሌሊት ምሥጢሩ ለዳንኤል በራእይ ተገለጠለት፤ ስለዚህ የሰማይን አምላክ እንዲህ ሲል አመሰገነ፦


ከዕለታት አንድ ቀን በአልጋዬ ላይ ተኝቼ ሳለ የሚያስፈራ ሕልምና የሚያስደነግጥ ራእይ አየሁ።


እርሱም በሚናገርበት ጊዜ ኅሊናዬን ስቼ በግንባሬ ወደ መሬት ተደፋሁ፤ እርሱ ግን ዳሰሰኝና ከመሬት አንሥቶ በእግሮቼ አቆመኝ።


እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ እኔ የምነግራችሁን አድምጡ! በመካከላችሁ ነቢያት ቢኖሩ ራሴን የምገልጥላቸው በራእይ ነው፤ በሕልምም አነጋግራቸዋለሁ፤


ወደ ሄሮድስም እንዳይመለሱ እግዚአብሔር በሕልም ስላስጠነቀቃቸው፥ ተመራማሪዎቹ በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ተመልሰው ሄዱ።


ከዚህም በላይ ጲላጦስ በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ፦ “በእርሱ ምክንያት ዛሬ ሌሊት በሕልም ብዙ ተሠቃይቻለሁና በዚያ በንጹሕ ሰው ላይ ምንም እንዳታደርግ” ስትል ላከችበት።


እግዚአብሔር በቀድሞ ዘመናት በተለያዩ መንገዶች፥ በነቢያት አማካይነት ለአባቶቻችን ብዙ ጊዜ ተናግሮ ነበር፤


跟着我们:

广告


广告