Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 33:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ሰው አያስተውልም እንጂ እግዚአብሔር በተለያየ መንገድ ይናገራል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ሰው ባያስተውለውም፣ እግዚአብሔር በተለያየ መንገድ ይናገራል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እግዚአብሔር በአንድም በሁለትም መንገድ ይናገራል፥ ሰው ግን አያስተውለውም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ልም ወይም በሌ​ሊት ራእይ፥ አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ የተ​ና​ገረ እን​ደ​ሆነ፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እግዚአብሔር በአንድ መንገድ በሌላም ይናገራል፥ ሰው ግን አያስተውለውም።

参见章节 复制




ኢዮብ 33:14
15 交叉引用  

እግዚአብሔር፥ ሌሊት በራእይ ተገለጠለትና “ያዕቆብ! ያዕቆብ!” ብሎ ጠራው። እርሱም “አቤት ጌታ ሆይ፥ እነሆ አለሁ” አለ።


እግዚአብሔር ምናሴንና ሕዝቡን በብርቱ ያስጠነቀቃቸው ቢሆንም እንኳ እነርሱ መስማትን እምቢ አሉ፤


“እነሆ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ነገር ለሰዎች መላልሶ ያደርጋል።


ሰዎች ከባድ እንቅልፍ በሚይዛቸውና በሚያስጨንቅ የሌሊት ቅዠት ጊዜ፥


አንድ ጊዜ፥ ወይም ሁለት ጊዜ ተናገርኩ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ከቶ አልናገርም። እግዚአብሔር


እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ተናግሮአል፤ ኀይል የእግዚአብሔር መሆኑን ሁለት ጊዜ ሰምቼአለሁ።


ጌታ ሆይ! ለሁሉም እንደየሥራው ስለምትከፍል ዘለዓለማዊ ፍቅር ያንተ ነው።


ወደ እኔ እንድትመጡ እጄን ዘርግቼ ጠራኋችሁ፤ እናንተ ግን ጥሪዬን አልተቀበላችሁም።


ዕውቀትን ጠላችሁ፤ እግዚአብሔርንም መፍራት አልወደዳችሁም።


እርሱም “እንግዲያውስ ወደዚህ ሕዝብ ሂድና ‘መስማትንስ ትሰማላችሁ፤ ነገር ግን አታስተውሉም፤ ማየትንም ታያላችሁ ነገር ግን ልብ አታደርጉም’ በላቸው” አለኝ።


የባቢሎን ንጉሥ ብልጣሶር በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት በአልጋው ላይ ተኝቶ ሳለ፤ ዳንኤል ሕልምና ራእይ አየ፤ ከዚያም በኋላ ያየውን ሕልም ጻፈ።


ስለዚህ በነቢዩ በኢሳይያስ እንዲህ ተብሎ የተጻፈው በእነርሱ ላይ ይፈጸማል፦ ‘መስማትንስ ትሰማላችሁ፤ ነገር ግን አታስተውሉም፤ ማየትንም ታያላችሁ፤ ነገር ግን ልብ አታደርጉም።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የማታስተውሉና ነቢያት የተናገሩትንም ሁሉ ከማመን ልባችሁ የዘገየ!


“ፍርዱም ይህ ነው፦ ብርሃን ወደ ዓለም መጣ፤ ሰዎች ግን ሥራቸው ክፉ ስለ ሆነ ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ወደዱ።


跟着我们:

广告


广告