ኢዮብ 32:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ቡዛዊው የባራኪ ልጅ ኤሊሁ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ በዕድሜዬ ከእናንተ ያነስኩ በመሆኔና እናንተም አዛውንት በመሆናችሁ፥ ኀፍረትና ፍርሀት ተሰምቶኝ ሐሳቤን ሳልገልጥ እስከ አሁን ቈይቼ ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ስለዚህ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ እንዲህ አለ፤ “እኔ በዕድሜ ታናሽ ነኝ፤ እናንተ ግን አዛውንቶች ናችሁ፤ ከዚህም የተነሣ የማውቀውን ለመናገር አልደፈርሁም፤ ፈርቼ ዝም አልሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 የቡዛዊውም የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ ተናገረ፤ እንዲህም አለ፦ “እኔ በዕድሜ ታናሽ ነኝ፥ እናንተ ግን ሽማግሌዎች ናችሁ፥ ስለዚህም ሰጋሁ፥ የማውቀውን እገልጥላችሁ ዘንድ ፈራሁ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤልዩስም መለሰ፥ እንዲህም አለ፥ “እኔ በዕድሜዬ ታናሽ ነኝ፥ እናንተ ግን ሽማግሌዎች ናችሁ፤ ስለዚህም ዕውቀቴን እገልጥላችሁ ዘንድ ፈርቼ ዝም አልሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 የቡዛዊውም የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ ተናገረ እንዲህም አለ፦ እኔ በዕድሜ ታናሽ ነኝ፥ እናንተ ግን ሽማግሌዎች ናችሁ፥ ስለዚህም ሰጋሁ፥ እውቀቴን እገልጥላችሁ ዘንድ ፈራሁ። 参见章节 |