Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 32:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በዚህ ጉዳይ ለማንም አላደላም፤ ማንንም አላቆላምጥም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ለማንም አላደላም፤ ሰውንም አላቈላምጥም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በማንም ሰው ፊት ግን አላደላም፥ ማንንም አላቈላምጥም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ከሰው የተ​ነሣ አላ​ፍ​ር​ምና፥ ከሟች ሰውም የተ​ነሣ አላ​ፈ​ገ​ፍ​ግ​ምና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ለሰው ፊት ግን አላደላም፥ ሰውንም አላቈላምጥም።

参见章节 复制




ኢዮብ 32:21
18 交叉引用  

እንዲሁም ንጉሥ ሆይ! ንጉሥ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ስለ ሆነና መልካሙን ከክፉው ለይቶ ስለሚያውቅ የተስፋ ቃልህ በሰላም እንድኖር ይረዳኛል ብዬ አስቤ ነው እንግዲህ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን!”


እርሱም ይህን ያደረገው ነገሮችን ሁሉ ለማስተካከል በማሰብ ነው፤ ንጉሥ ሆይ! አንተ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ጥበበኛ ነህ፤ የሚሆነውንም ነገር ሁሉ ታውቃለህ።”


በስውር አድልዎ ብታደርጉ በእውነት እግዚአብሔር ይገሥጻችኋል።


ለእርሱ ታደሉለታላችሁን? ለእርሱስ ጥብቅና ትቆማላችሁን?


ተናግሬ ይውጣልኝ፤ በአንደበቴ መልስ መስጠት አለብኝ።


እኔ ሰውን ማቈላመጥ አይሆንልኝም፤ ይህንንም ባደርግ ፈጣሪዬ በፍጥነት ይቀጣኝ ነበር።”


ቃሎቼ የልቤን ቅንነት ይገልጣሉ፤ ምላሶቼም እውነቱን ይናገራሉ።


ሁሉም የእጁ ሥራዎች ስለ ሆኑ፤ እርሱ ለመኳንንቱ አያደላም ባለጸጋውን ከድኻው አይለይም።


“እስከ መቼ ትክክል ያልሆነ ፍርድ ትፈርዳላችሁ? እስከ መቼ ለክፉዎች ታዳላላችሁ?


የጥበበኞች ተጨማሪ አባባሎች፦ በዳኝነት ማዳላት ስሕተት ነው፤


ሰውን ከማቈላመጥ ይልቅ እየመከረ የሚገሥጸውን ሰው በመጨረሻ ያመሰግነዋል።


“የፍርድ ውሳኔ በምትሰጡበት ጊዜ ታማኞችና ትክክለኞች ሁኑ፤ ለሁሉም በትክክል ፍረዱ እንጂ ለድኻው ስለ ድኽነቱ አድልዎ አታድርጉለት፤ ባለጸጋውንም ስለ ሀብቱ ብዛት አትፍሩት።


የእኔን ሥርዓት ባለመከታተል በሕግ ጉዳይ አድልዎ ስለምትፈጽሙ እኔ ደግሞ በሕዝብ ሁሉ ፊት እንድትናቁና እንድትዋረዱ አደርጋችኋለሁ።”


የእነርሱንም ደቀ መዛሙርት ከሄሮድስ ሰዎች ጋር ወደ ኢየሱስ ልከው፥ “መምህር ሆይ! አንተ እውነተኛ መሆንህንና የእግዚአብሔርን መንገድ በእውነት እንደምታስተምር እናውቃለን፤ ሰውንም በመፍራት የምታደርገው ነገር የለም፤ ለሰውም አታዳላም” ካሉት በኋላ፥ እንዲህ ብለው ጠየቁት።


በምትሰጡትም ውሳኔ አድልዎ አታድርጉ፤ ስለ ማንኛውም ታላቅም ሆነ ታናሽ ሰው ያለ አድልዎ በእኩልነት ፍረዱ። ፍርድ የእግዚአብሔር ስለ ሆነ ማንንም አትፍሩ፤ ለእናንተ የሚከብድባችሁ ነገር ቢኖር ወደ እኔ አምጡት፤ እኔም ውሳኔ እሰጥበታለሁ፤’


ፍርድን አታጣምም፤ ፊት አይተህ አታድላ፤ አታታል፤ ጉቦ የጥበበኞችን ዐይን ስለሚያሳውርና የተጣመመ ፍርድ ስለሚያሰጥ ጉቦ አትቀበል።


跟着我们:

广告


广告