Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 31:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 “ድኾች የሚለምኑትን ከልክዬ አላውቅም፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸውንም ሴቶች ከማጽናናት አልተቈጠብኩም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 “ለድኻ የሚያስፈልገውን ከልክዬ ከሆነ፣ ወይም የመበለቲቱን ዐይን አፍዝዤ ከሆነ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 “ድሀውን ከሚያስፈልገው ከልክዬ፥ የመበለቲቱን ዐይን አጨልሜ እንደሆነ፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 “ድሆች የሚ​ሹ​ትን እን​ዳ​ያ​ገኙ አድ​ርጌ እንደ ሆነ፥ የመ​በ​ለ​ቲ​ቱ​ንም ዐይን አጨ​ልሜ እንደ ሆነ፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ድሀውን ከልመናው ከልክዬ፥ የመበለቲቱን ዓይን አጨልሜ እንደ ሆነ፥

参见章节 复制




ኢዮብ 31:16
23 交叉引用  

ይህም የሚሆነው ድኻን ስለ ጨቈነና ያልሠራውንም ቤት በግፍ ስለ ወሰደ ነው።


ለድኾች ተስፋ ይሰጣል፤ ዐመፅንም ከምድረ ገጽ ያጠፋል።


ለችግረኞች በልግሥና ይሰጣል፤ ቸርነቱም የማያቋርጥ ነው፤ ኀይልንና ክብርን ይጐናጸፋል።


አዳኝነትህንና እውነተኛ ቃል ኪዳንህን በመጠባበቅ ዐይኖቼ ደከሙ።


“መቼ ታጽናናኝ ይሆን?” ብዬ የተስፋ ቃልህን በመጠባበቅ ዐይኖቼ ደከሙ።


ከመጮኼ ብዛት የተነሣ ደከምኩ፤ ጒሮሮዬም ቈሰለ፤ አምላኬን በመጠባበቅ ዐይኖቼ ፈዘዙ።


ባልዋ የሞተባትን መበለት ወይም አባትና እናት የሞቱበትን ድኻ ዐደግ አታጒላሉ።


ምንም ስለሌላቸው፥ ድኾችን አትበዝብዝ፤ የተጨቈኑትንም ሰዎች በፍርድ ሸንጎ አታጒላላ፤


ለድኾችና ለችግረኞች ትለግሣለች።


የድኾች መብት እንዳይከበርና የተበደሉ ፍትሕ እንዳያገኙ የምታደርጉበት ዘዴ ይኸው ነው፤ በዚሁ ዘዴ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶችና አሳዳጊ የሌላቸውን የሙት ልጆች ንብረት ትነጥቃላችሁ።


እንደ ሽመላ እጮኽ ነበር፤ እንደ ርግብ የሐዘን ድምፅ አሰማ ነበር፤ ወደ ሰማይም አሻቅቤ ከመመልከቴ የተነሣ፥ ዐይኖቼ በጣም ደክመው ነበር። ጌታ ሆይ! እባክህን ከዚህ ሁሉ መከራ አድነኝ!


በከንቱ ረዳት በመጠበቅ ዐይናችን ደከመ ሊታደግ ከማይችል ሕዝብ በጒጒት ርዳታ ጠበቅን።


ማንንም ባይጨቊን፥ ወይም የሰውን ሀብት ባይቀማ፥ ገንዘብ ሲያበድር በመያዣ የወሰደውን ባያስቀር፥ ለተራበ ቢያበላ፥ ለታረዘም ቢያለብስ፥


“በአቅራቢያህ የሚኖር እስራኤላዊ ወገንህ ደኽይቶ ራሱን መርዳት የማይችል ቢሆን በአጠገብህ መኖር ይችል ዘንድ ላስጠጋኸው መጻተኛ በምታደርገው ዐይነት የሚያስፈልገውን ሁሉ በፈቃድህ አድርግለት።


“ለታይታ በምታቀርቡት ረዥም ጸሎት እያመካኛችሁ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች መተዳደሪያ የምትጨርሱ እናንተ ግብዞች የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ስለዚህ እናንተ የባሰ ፍርድ ይደርስባችኋል።]


ሁለት መክሊት የተቀበለውም እንዲሁ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፈ።


ይህም ድኻ፥ ከሀብታሙ ማእድ የሚወድቀውን ፍርፋሪ ለመመገብ ይመኝ ነበር፤ ውሾችም እየመጡ ቊስሉን ይልሱ ነበር።


ስለዚህ በአንጾኪያ የሚኖሩ ምእመናን በይሁዳ ለሚኖሩ ወንድሞች እያንዳንዳቸው እንደየችሎታቸው በማዋጣት ርዳታ እንዲላክ ወሰኑ።


ብቻ በመካከላቸው ያሉትን ድኾች እንድናስታውስ ዐደራ አሉን፤ ይህም እኔ በትጋት ያደረግኹት ነገር ነው።


ዐይንህ እያየ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ለባዕዳን ይሰጣሉ፤ የልጆችህን መመለስ በከንቱ በመጠባበቅ ዐይንህ ሲንከራተት ይኖራል፤ ነገር ግን ምንም ለማድረግ አትችልም።


በእግዚአብሔር አብ ፊት ንጹሕና ያልረከሰ ሃይማኖት “አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች፥ እንዲሁም ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በችግራቸው መርዳት፥ ራስንም ከዓለም ርኲሰት መጠበቅ ነው።”


跟着我们:

广告


广告