Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 30:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ለተቸገሩ ሰዎች አላለቀስኩምን? ለድኾችስ አልተጨነቅኹምን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 በመከራ ውስጥ ላሉት አላለቀስሁምን? ለድኾችስ ነፍሴ አላዘነችምን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ለተጨነቁት አላለቀስሁምን? ለችግረኛስ ነፍሴ አላዘነችምን?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ረዳት ለሌ​ለው ሰው አለ​ቀ​ስሁ የተ​ቸ​ገረ ሰውን ባየሁ ጊዜ ጮኽሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ጭንቅ ቀን ላገኘው ሰው አላለቀስሁምን? ለችግረኛስ ነፍሴ አላዘነችምን?

参见章节 复制




ኢዮብ 30:25
20 交叉引用  

ድኾችን በመጸየፍ ከየመንገዱ ያባርራሉ፤ ከፊታቸውም ሸሽተው እንዲደበቁ ያደርጋሉ።


ይህም የሆነው የድኾችን ጩኸት ሰምቼ እታደጋቸውና፥ ወላጆቻቸው የሞቱባቸውንም ልጆች እረዳቸው ስለ ነበረ ነው።


ለድኾች አባት፥ ለማላውቃቸውም ሰዎች ጠበቃ ነበርኩ።


በእርግጥ ቤተሰቦቼ ‘ከእርሱ ዘንድ ምግብ በልቶ ያልጠገበ ከቶ ማነው?’ ብለው ይመሰክራሉ።


እግዚአብሔር ሆይ! አንድም ታማኝ ሰው ስላልቀረ እባክህ እርዳን፤ ታማኞች ሰዎች በሰው ዘር መካከል ጠፍተዋል።


ሰዎችን የሚንቅ ኃጢአተኛ ነው፤ ለድኾች የሚራራ ግን የተባረከ ነው፤


ድኾችን ማስጨነቅ ፈጣሪን መናቅ ነው፤ ለድኾች ቸርነትን ማድረግ ግን እግዚአብሔርን እንደ ማክበር ይቈጠራል።


በድኾች ብታፌዝ የፈጠራቸውን እግዚአብሔርን እንደ ሰደብክ ይቈጠራል፤ በሌላው ሰው ላይ በሚደርሰው መከራ ብትደሰት አንተም ትቀጣለህ።


ለድኾች የሚሰጥ ለእግዚአብሔር እንዳበደረ ይቈጠራል፤ እግዚአብሔርም የመልካም ሥራውን ዋጋ ይከፍለዋል።


በአራጣ በማበደርና ሰዎችን በመበዝበዝ የሚከብር ሰው ሀብቱ ሁሉ ለድኾች ልግሥና ለሚያደርግ ሰው ይተላለፋል።


አናዳምጥም ብትሉ ግን ስለ ትዕቢታችሁ ተደብቄ አለቅሳለሁ፤ የእግዚአብሔር ሕዝብ ምርኮኞች ሆነው በመወሰዳቸውም ምርር ብዬ አለቅሳለሁ፤ እንባዬም ባለማቋረጥ ይፈስሳል።


ታዲያ የደግ ሥራ ዋጋው ክፉ ነገር ማድረግ ነውን? አንተ በእነርሱ ላይ እንዳትቈጣ እኔ በፊትህ ቆሜ ስለ እነርሱ እንደማለድኩህ አስብ፤ እነርሱ ግን እነሆ እኔ የምወድቅበትን ጒድጓድ ቈፈሩ።


ስለዚህ ንጉሥ ሆይ! በበኩሌ የምመክርህን ስማ፤ ኃጢአት መሥራትን ትተህ መልካም ሥራ መሥራትን አዘወትር፤ ክፋትን ትተህ ለተጨቈኑ ሰዎች ራራላቸው፤ ይህን ብታደርግ በሰላም የመኖር ዕድሜህ ይረዝምልህ ይሆናል።”


ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ቀርቦ፥ ከተማይቱን በተመለከተ ጊዜ፥ አለቀሰላት።


ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ።


ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ።


ይህም፦ “ለድኾች በልግሥና ሰጠ፤ ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።


跟着我们:

广告


广告