Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 28:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ዝናብና ለነጐድጓዳዊ መብረቅ ሥርዓትን በደነገገ ጊዜ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ለዝናብ ሥርዐትን፣ ለነጐድጓድም መንገድን ባበጀ ጊዜ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ለዝናብም ሥርዓትን፥ ለነጐድጓድ መብረቅም መንገድን ባደረገ ጊዜ፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 እነ​ዚ​ህን በፈ​ጠረ ጊዜ እን​ዲሁ ዐውቆ ቈጠ​ራ​ቸው። ለዝ​ናም ሥር​ዐ​ትን ለነ​ጐ​ድ​ጓድ መብ​ረ​ቅም መን​ገ​ድን አደ​ረገ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ለዝናብም ሥርዓትን፥ ለነጐድጓድ መብረቅም መንገድን ባደረገ ጊዜ፥

参见章节 复制




ኢዮብ 28:26
20 交叉引用  

እግዚአብሔር ጥበብን ተመለከታት ገምግሞም አከበራት፤ መርምሮም አጸናት።


የእግዚአብሔርን ታላቅነት መርምረን ልንደርስበት አንችልም፤ የዘመኑንም ልክ መመርመር አይቻልም።


“እግዚአብሔር ውሃን ከባሕር ወደ ላይ ይስባል፤ ከሰማይም ያዘንበዋል።


ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ደመናውን እንዴት እንደሚዘረጋና በነጐድጓድም ውስጥ ሆኖ እንዴት እንደሚናገር፥ ማን ሊረዳ ይችላል?


መብረቅን በእጁ ይይዛል፤ ወደተወሰነለትም አቅጣጫ እንዲሄድ ያዘዋል።


ደመና ውሃ እንዲሸከም ያደርጋል፤ በውስጡም መብረቅን ያበርቃል።


ከአፉ የሚወጣውን ድምፅ ስሙ እንደ ነጐድጓድ የሚያጒረመርመውን ቃሉን አድምጡ።


መብረቁን ከሰማይ በታች ሁሉ ያሠራጫል፤ እስከ ምድር ዳርቻም ድረስ ይልካል።


ከዚህም በኋላ ኀይለኛ ድምፁን ያስገመግማል፤ የሚያስፈራ ድምፁንም እንደ ነጐድጓድ ያሰማል፥ የመብረቁም ብልጭታ ደጋግሞ ይታያል። በግርማዊ ድምፁም ነጐድጓድን ያሰማል፤ ድምፁን በሚያሰማበት ጊዜ መብረቁን አያግድም።


በረዶ በምድር ላይ እንዲወርድ ያደርጋል፤ ብርቱ ዝናብም እንዲዘንብ ያዛል።


“ለዝናብ መውረጃን ያዘጋጀለት፥ ነጐድጓድ ለተቀላቀለበት ውሽንፍርም መንገድ ያበጀለት ማነው?


እንዲሁም ማንም በሌለበት ምድር፥ ሰው በማይኖርበት ምድረ በዳ፥


ዝናብ እንዲዘንብ የሚያደርግ ማነው? ጠፍና ባድማ የሆነውን መሬት ረስርሶ ምድሩንም ሣር እንዲያበቅል ያደረገው ማነው?


ዝናብ ያዘለ ደመናን ከምድር ዳርቻ ያመጣል፤ በዝናብ ጊዜ መብረቅ እንዲኖር ያደርጋል፤ ነፋስንም ከቦታው ያወጣዋል።


እሳትና በረዶ፥ ዐመዳይና ደመና፥ ትእዛዙን የምትፈጽሙም ብርቱዎች ነፋሳት እግዚአብሔርን አመስግኑ።


“እግዚአብሔር ከሁሉ በፊት ፈጠረኝ፤ ከጥንት ጀምሮ የሥራው ተቀዳሚ አደረገኝ።


ከአሕዛብ አማልክት መካከል አንዱ እንኳ ዝናብ ማዝነብ አይችልም፤ ሰማይም በራሱ ፈቃድ ካፊያ አያወርድም፤ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! ይህን ሁሉ የምታደርግ አንተ ስለ ሆንክ እኛ ተስፋ የምናደርገው በአንተ ነው።


አዝመራችሁ ከመድረሱ ከሦስት ወር በፊት ዝናብ እንዲቋረጥ አደረግሁ፤ በአንድ ከተማ ሲዘንብ በሌላው ከተማ እንዳይዘንብ አደረግሁ፤ ለአንዱ እርሻ ሲዘንብለት ሌላው እርሻ ዝናብ አጥቶ ደረቀ።


እግዚአብሔር በበልግ ወራት ዝናብ እንዲሰጣችሁ ለምኑት፤ ዝናብ ያዘለ ደመናን የሚልክ እግዚአብሔር ነው፤ ዝናብንና የመስክ አትክልትን ለሁሉም የሚሰጥ እርሱ ነው።


跟着我们:

广告


广告