Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 28:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እርሱም የምድርን ዳርቻ ሁሉ ይመለከታል፤ ከሰማይ በታች ያለውን ሁሉ ያያል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እርሱ የምድርን ዳርቻ ይመለከታልና፤ ከሰማይ በታች ያለውንም ሁሉ ያያል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 እርሱም የምድርን ዳርቻ ይመለከታል፥ ከሰማይም በታች ያለውን ሁሉ ያያል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 እር​ሱም በሰ​ማይ ያለ​ውን ይመ​ለ​ከ​ታል፥ በም​ድ​ርም ያለ​ውን ሁሉ ያው​ቃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 እርሱም የምድርን ዳርቻ ይመለከታል፥ ከሰማይም በታች ያለውን ሁሉ ያያል።

参见章节 复制




ኢዮብ 28:24
15 交叉引用  

እግዚአብሔር መላውን ዓለም አተኲሮ በመመልከት፥ በሙሉ ልባቸው በእርሱ ለሚተማመኑት ሁሉ ብርታትን ይሰጣቸዋል፤ እንግዲህ አንተ የሞኝነት ሥራ ስለ ፈጸምክ ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይለይህም፤”


የአንተ ዐይን እንደ ሰው ዐይን ነውን? ወይስ የምታየው እንደ ሰው ነውን?


እግዚአብሔር የማይጠቅሙ ሰዎችን ያውቃቸዋል፤ በደልን በሚያይበት ጊዜ ዝም ብሎ አይመለከትም።


እግዚአብሔር የማደርገውን ሁሉ አያይምን? እርምጃዎቼንስ አይቈጣጠርምን?


መብረቁን ከሰማይ በታች ሁሉ ያሠራጫል፤ እስከ ምድር ዳርቻም ድረስ ይልካል።


ንጋት በምድር ላይ ብርሃን እንዲያሳይ፥ ክፉ ሰዎችንም ከተደበቁበት ቦታ እንዲያጋልጥ ትእዛዝ ሰጥተህ ታውቃለህን?


ዓለም ምን ያኽል ትልቅ እንደ ሆነች ማወቅ ትችላለህን? እስቲ ይህን ሁሉ ታውቅ እንደ ሆነ ንገረኝ።


ከሰማይ በታች ያለው ነገር ሁሉ የእኔ ነው፤ ታዲያ፥ እንድመልስለት ለእኔ ያበደረ ማነው?


እግዚአብሔር በተቀደሰ መቅደሱ ነው፤ ዙፋኑም በሰማይ ነው፤ የሰውን ልጆች ይመለከታል። አተኲሮም በማየት ዐይኖቹም ይመረምሩአቸዋል።


ነገር ግን ሰማይንና ምድርን ወደ ታች ይመለከታል።


በኀይሉ ለዘለዓለም ይገዛል፤ በዐይኑም መንግሥታትን አተኲሮ ያያል፤ ስለዚህ ዐመፀኞች በእርሱ ላይ ባይነሡ ይሻላቸዋል።


እግዚአብሔር በየቦታው የሚደረገውን ነገር ሁሉ ያያል። መልካምም ሆነ ክፉ ድርጊትን ይመለከታል።


ትንሽ ነገር የሚደረግበትን ቀን የናቀ ቱምቢውን በዘሩባቤል እጅ ሲያይ ይደሰታል፤ እነዚህ ሰባቱ መቅረዞች ዓለምን የሚያካልሉ የእግዚአብሔር ዐይኖች ናቸው።”


ከዚህ በኋላ በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች መካከል፥ በሽማግሌዎችም መካከል የታረደ የሚመስል በግ ቆሞ አየሁ፤ ይህ በግ ሰባት ቀንዶችና ሰባት ዐይኖች ነበሩት፤ እነርሱ ወደ ዓለም ሁሉ የተላኩ ሰባቱ የእግዚአብሔር መንፈሶች ናቸው።


跟着我们:

广告


广告