Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 22:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ያዋርዳል፤ ትሑታንን ግን ያድናቸዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ሰዎች ቢዋረዱና አንተ፣ ‘ከፍ አድርጋቸው’ ብትል፣ እርሱ ዝቅ ያሉትን ያድናል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ቢያዋርዱ፥ አንተ ‘መነሣት አለ’ ትላለህ፥ ትሑቱንም ሰው ያድነዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ራስ​ህን ብታ​ዋ​ርድ ሰውም ኰራ​ብኝ ብትል፥ ራሱን የሚ​ያ​ዋ​ር​ደ​ውን ሰው ያድ​ነ​ዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ቢያዋርዱህ አንተ ከፍ ከፍ ትላለህ፥ ትሑቱንም ሰው ያድነዋል።

参见章节 复制




ኢዮብ 22:29
17 交叉引用  

እግዚአብሔር ደጋግ ሰዎችን ይጠብቃል፤ እንደ ነገሥታትም በዙፋን ላይ ያስቀምጣቸዋል፤ ለዘለዓለምም ከፍ ከፍ ያደርጋቸዋል።


የተዋረዱትን በክብር ከፍ ያደርጋቸዋል፤ ያዘኑትንም በማጽናናት ደስ ያሰኛቸዋል።


ከሁሉ በላይ ከፍ ያልክ ሆነህ ሳለ፥ ትሑታንን ትንከባከባለህ፤ ትዕቢተኞችን ግን ከሩቅ ሆነህ ትመለከታቸዋለህ።


ትምክሕተኛነት ወደ ውድቀት ያደርስሃል፤ ትሑት ከሆንክ ግን ትከበራለህ።


ከፍተኛውና ከሁሉ የላቀው፥ ለዘለዓለም የሚኖር ቅዱሱ እንዲህ ይላል፦ “እኔ በተቀደሰና በከፍተኛ ቦታ፥ እንዲሁም ልባቸው ከተሰበረና መንፈሳቸው ትሑት ከሆኑት ጋር እኖራለሁ፤ ይኸውም ትሑት መንፈሳቸውንና የተሰበረ ልባቸውን ለማደስ ነው።


እነዚህን ሁሉ ነገሮች የፈጠርኩ እኔ ነኝ፤ ስለዚህ ሁሉም የእኔ ናቸው፤ እኔ የምመለከተው ልባቸው ወደ ተሰበረ፥ ትሑት መንፈስ ወዳላቸውና፥ ቃሌንም ወደሚያከብሩ ነው።


ራሱን ከፍ የሚያደርግ ይዋረዳል፤ ራሱንም ዝቅ የሚያደርግ ከፍ ይላል።”


ታላላቅ ገዢዎችን ከዙፋናቸው አውርዶአቸዋል፤ ዝቅተኞችን ግን በክብር ከፍ አድርጎአቸዋል።


ራሱን ከፍ የሚያደርግ ይዋረዳል፤ ራሱን የሚያዋርድ ግን ከፍ ይላል።”


ሆኖም መጽሐፍ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ስለሚል እግዚአብሔር የሚሰጠው ጸጋ ከሁሉም ይበልጣል።


እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ታዘዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።


跟着我们:

广告


广告