Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 22:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ዕቅድህ ሁሉ ይሳካልሃል፤ መንገድህ ሁሉ ብርሃን ይሆንልሃል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ያሰብኸው ይከናወንልሃል፤ በመንገድህም ላይ ብርሃን ይበራል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 በጉዳዮችም ላይ ትመክራለህ፥ እርሱም ይሳካልሃል፥ ብርሃንም በመንገድህ ላይ ይበራል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 የጽ​ድ​ቅ​ህ​ንም ብድ​ራት ይሰ​ጥ​ሃል። ብር​ሃ​ንም በመ​ን​ገ​ድህ ላይ ይበ​ራል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ነገርንም ትመክራለህ፥ እርሱም ይሳካልሃል፥ ብርሃንም በመንገድህ ላይ ይበራል።

参见章节 复制




ኢዮብ 22:28
15 交叉引用  

ሕይወትህ ከቀትር ፀሐይ ይበልጥ ይበራል፤ ጨለማው እንደ ማለዳ ብርሃን ይሆናል።


ያን ጊዜ በጨለማ ውስጥ ስሄድ፥ እግዚአብሔር መብራቱን እያበራልኝ በብርሃን እራመድ ነበር።


ወደ ሙታን ዓለም ከመውረድም አዳነኝ፤ እነሆ፥ አሁን በሕይወት ተገኝቼ ብርሃንን አያለሁ።’


እርሱም፦ ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፥ ቅጠሏም እንደማይረግፍ፥ በፈሳሽ ውሃ ዳር እንደ ተተከለች ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሥራ ሁሉ ይሳካለታል።


ምሕረትና ቸርነት፥ ቅንነትም ለሚያደርግ ለደግ ሰው በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይወጣለታል።


የልብህን ምኞት ይስጥህ፤ ሐሳብህን ሁሉ ይፈጽምልህ፤


እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! በረከትህ ከእኛ ጋር ይሁን፤ የምናደርገውንም ሁሉ አሳካልን።


ብርሃን ለደጋግ ሰዎች፥ ደስታም ለልበ ቅኖች ይወጣላቸዋል።


የደጋግ ሰዎች መንገድ እንደ ንጋት ብርሃን ነው፤ የቀኑ ሙሉ ብርሃን እስኪሆን ድረስ ብርሃኑ እየጨመረ ይሄዳል።


ከመንገድ ወጥታችሁ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ብትባዝኑ ከበስተኋላችሁ “ትክክለኛው መንገድ ይህ ነው! በዚህ ሂድ” የሚለውን ድምፅ ትሰማላችሁ።


እግዚአብሔር አስቀድሞ የወሰነው ካልሆነ በትእዛዙ አንድን ነገር ማስደረግ የሚችል ማነው?


ለእናንተ ስሜን ለምታከብሩ የጽድቅ ፀሐይ ይወጣላችኋል፤ ፈውስንም ይሰጣችኋል። ከጒረኖ እንደ ተለቀቀ ጥጃ ትቦርቃላችሁ።


አምናችሁ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ታገኛላችሁ።”


እንደገናም ኢየሱስ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ እኔን የሚከተል ሁሉ የሕይወት ብርሃን ያገኛል፤ በጨለማም አይመላለስም” ሲል ተናገራቸው።


ይልቁንስ እናንተ ማለት የሚገባችሁ “ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር ይህን ወይም ያን እናደርጋለን” ነው።


跟着我们:

广告


广告