Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 21:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ሁሉም ወደ መቃብር በአንድ ላይ ወርደው ዐፈር ይሆናሉ፤ ትልም ይወርሳቸዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ሁለቱም በዐፈር ውስጥ አንድ ላይ ይተኛሉ፤ ትልም ይወርሳቸዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በአፈር ውስጥ በአንድ ላይ ይተኛሉ፥ ትልም ይከድናቸዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ሁሉም በአ​ፈር ውስጥ በአ​ንድ ላይ ይተ​ኛሉ፤ ትሎ​ችም ይሸ​ፍ​ኗ​ቸ​ዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በአፈር ውስጥ በአንድ ላይ ይተኛሉ፥ ትልም ይከድናቸዋል።

参见章节 复制




ኢዮብ 21:26
12 交叉引用  

መቃብርን ‘አባቴ’ ብዬ እጠራዋለሁ፤ የሚበሉኝንም ትሎች ‘እናቴና እኅቴ’ እላቸዋለሁ።


ቆዳዬ ተበልቶ ቢያልቅም፥ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንደማየው ዐውቃለሁ።


ኀይል የተሞላው የወጣትነት ሰውነቱ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ዐፈር ይሆናል።


ሌሎች ግን መሪር ሐዘን ሳይለያቸው፥ በችግር እንደ ተቈራመዱ መልካም ነገር ሳያገኙ ይሞታሉ።


“እነሆ፥ እኔን ለመበደል በማሰብ በአእምሮአችሁ ያቀዳችሁትን ተንኰል ዐውቃለሁ።


እናቶቻቸው ሁሉ ይረሱአቸዋል፤ ሥጋቸውንም ትል ይበላዋል፤ ክፉ ሰዎች አይታወሱም፤ ነገር ግን እንደ ዛፍ ይሰባበራሉ።


አሁን በሰላም በተጋደምኩ፥ አንቀላፍቼም ዕረፍት ባገኘሁ ነበር።


እነዚህ እንደ በጎች እንዲሞቱና እንዲቀበሩ ይደረጋሉ፤ እረኛ በጎችን እንደሚመራ ሞትም እነዚህን ወደ መቃብር ይመራል፤ ትክክለኞች ሰዎች በማለዳ በመቃብራቸው ላይ ይመላለሳሉ፤ ሥጋቸውም በመቃብር ውስጥ ይበሰብሳል፤ የሙታን ዓለምም መኖሪያቸው ይሆናል። ደጋግ ሰዎችም በማለዳ ተነሥተው በእነርሱ ላይ ሥልጣናቸውን ያሳያሉ።


ምንም ዐይነት ልዩነት ሳይደረግ ለጻድቅና ለኃጢአተኛ ለደግና ለክፉ፥ ለንጹሓንና ንጹሓን ላልሆኑ መሥዋዕት ለሚያቀርቡትና ለማያቀርቡትም የሚገጥማቸው ዕድል አንድ ዐይነት ነው፤ ይኸውም ደጉ ሰው ከኃጢአተኛው የተሻለ ዕድል የለውም፤ መሐላን የሚፈራው መሐላን ከሚደፍረው ሰው ተለይቶ አይታይም።


የሁሉም ዕድል ፈንታው አንድ ዐይነት ነው፤ ይህም በዓለም እንደሚደረገው እንደማንኛውም ነገር ሁሉ እጅግ የከፋ ነው፤ ሰዎችም በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ አእምሮአቸው በክፋትና በእብደት የተሞላ ሆኖ በመጨረሻ ይሞታሉ።


ቀድሞ ስለ ክብርህ በመሰንቆ ይዘመርልህ የነበረው ቆመ፤ አሁን አንተ በትዕቢትህ ወደ ሙታን ዓለም ወረድክ። ስለዚህ አልጋህ ምስጥ፥ ልብስህም የትል መንጋ ሆኖአል።’ ”


跟着我们:

广告


广告