Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 19:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በእውነት እናንተ ራሳችሁን ከፍ ከፍ አድርጋችሁ፥ የእኔን መዋረድ የመከራከሪያ ነጥብ ታደርጉታላችሁ

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ነገር ግን ራሳችሁን በእኔ ላይ ከፍ ብታደርጉ፣ መዋረዴንም እኔን ለመሞገት ብትጠቀሙበት፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 በእውነትም ብትኩራሩብኝ፥ በመዋረዴም ብታሳብቡ፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ወዮ​ልኝ! አፋ​ች​ሁን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ ታደ​ር​ጋ​ላ​ች​ሁና፤ ትጓ​ደ​ዱ​ብ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ትዘ​ል​ፉ​ኛ​ላ​ች​ሁም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 በእውነትም ብትጓደዱብኝ፥ መዋረዴን በእኔ ላይ ብትከራከሩ፥

参见章节 复制




ኢዮብ 19:5
16 交叉引用  

እነርሱም “ተማርከው ወደ ባቢሎን ሳይወሰዱ የቀሩትና በሕይወት ያሉት አይሁድ በታላቅ ችግርና ኀፍረት ላይ ወድቀው ይገኛሉ፤ የኢየሩሳሌምም ቅጽሮች ፈራርሰው ወድቀዋል፤ የቅጽር በሮቹም በእሳት ጋይተዋል” ሲሉ መለሱልኝ።


በእርግጥ ተሳስቼ ከሆነ፥ ስሕተቱ የሚጐዳው ራሴን ብቻ ነው።


በእኔ መከራ ተደስተው ትኲር ብለው በንቀት የሚመለከቱኝ ሁሉ ይፈሩ፤ ግራም ይጋቡ፤ በእኔ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ ሁሉ ኀፍረትንና ውርደትን ይልበሱ።


“ጠላቶቼ እኔን በንቀት ዐይን እንዲመለከቱኝ ወይም እግሬን ሲያዳልጠው ራሳቸውን ከፍ እንዲያደርጉ አታድርግ!” ብዬ እለምናለሁ።


እኔን ድል በማድረጋቸው እንደ ተደሰቱ አይቀሩም፤ አንተም በእኔ ደስ እንደ ተሰኘህ ዐውቃለሁ።


የሚሰድበኝ ጠላት አይደለም፤ ጠላት ቢሆንማ ኖሮ በታገሥኩ ነበር። የሚታበይብኝም ባለጋራ አይደለም፤ ባለጋራ ቢሆንማ ኖሮ ከፊቱ በተሰወርኩ ነበር።


ይህን ሁሉ የምታደርግብኝ አንተ ግን ከእኔ ከራሴ የማልለይህ፥ ጓደኛዬ፥ የቅርብ ወዳጄ ነህ።


በዚያን ጊዜ ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይዘው “በምግብም ሆነ በልብስ ራሳችንን ችለን እንተዳደራለን፤ ‘ባል የላቸውም’ ተብለን ከመሰደብ እንድንድን የአንተ ሚስቶች ተብለን እንድንጠራ ብቻ ፍቀድልን” ብለው ይለምኑታል።


ጠላቴ ሆይ! እኔ ብወድቅም እንኳ እንደገና እነሣለሁና በእኔ ደስ አይበልህ፤ አሁን በጨለማ ውስጥ ብሆንም እግዚአብሔር ያበራልኛል።


የሞአብና የዐሞን ሕዝብ በሠራዊት አምላክ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ስላፌዙና ስለ ዛቱ ይህ ቅጣት የሚደርስባቸው ለትዕቢታቸው አጸፋ የሚከፈል ዕድል ፈንታቸው ስለ ሆነ ነው።


“እኔ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ለይሁዳ ነገድ ድልን አጐናጽፋለሁ፤ ይህንንም የማደርገው የዳዊት ልጆች ክብርና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ክብር ከሌሎቹ የይሁዳ ነገድ ተወላጆች ከፍ ከፍ እንዳይል ነው።


“ጌታ ይህን መልካም ነገር አደረገልኝ፤ በሰዎች መካከል የነበረብኝን ነቀፌታ አስወገደልኝ።”


ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን “መምህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕውር ሆኖ የተወለደው በማን ኃጢአት ነው? በራሱ ኃጢአት ነውን ወይስ በወላጆቹ?” ሲሉ ጠየቁት።


እነርሱም “ሁለንተናህ በኃጢአት ተወርሶ የተወለድክ! አንተ እኛን ልታስተምር ነውን?” አሉና ከምኲራብ አስወጡት።


እግዚአብሔርም ልጅ ስላልሰጣት ጣውንትዋ ጵኒና ሐናን የሚያስቈጣ ነገር በመፈለግ ታበሳጫት ነበር፤


跟着我们:

广告


广告