Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 19:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 “እግዚአብሔር ወንድሞቼ ከእኔ እንዲርቁ አደረገ፤ የሚያውቁኝም ሰዎች ሁሉ ባይተዋር አደረጉኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “ወንድሞቼን ከእኔ አርቋል፤ ከሚያውቁኝም ተገለልሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 “ወንድሞቼን ከእኔ ዘንድ አራቀ፥ የሚያውቁኝም አጥብቀው ተለዩኝ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 “ወን​ድ​ሞች ተለ​ዩኝ፥ ከእኔ ይልቅ ባዕ​ዳ​ንን ወደዱ። ጓደ​ኞ​ችም አላ​ዘ​ኑ​ል​ኝም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ወንድሞቼን ከእኔ ዘንድ አራቀ፥ የሚያውቁኝም አጥብቀው ተለዩኝ።

参见章节 复制




ኢዮብ 19:13
20 交叉引用  

ወዳጆቼ በንቀት ይመለከቱኛል፤ እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር አለቅሳለሁ።


አምላክ ሆይ! ከሰውነት ውጪ አደረግኸኝ፤ ቤተሰቤንም ሁሉ አጠፋህብኝ።


በዚህ ጊዜ የኢዮብ ወንድሞች፥ እኅቶችና ቀድሞ የሚያውቁት ሰዎች ሁሉ ሊጐበኙት መጡ፤ በቤቱም ከእርሱ ጋር ተመገቡ፥ ሐዘናቸውን በመግለጥ እግዚአብሔር ስላደረሰበት ብርቱ መከራ አጽናኑት፤ እያንዳንዳቸውም የብርና የወርቅ ቀለበት ስጦታ አደረጉለት።


ወንድሞቼ ግን ጐርፉ ከወረደ በኋላ እንደሚደርቁና እንደማያስተማምኑ ወንዞች አታላዮች ናቸው።


የተማመኑበትን ወንዝ ደርቆ ሲያገኙ ተስፋ ይቈርጣሉ፤ ወደ ቦታውም ሲደርሱ ይበሳጫሉ።


እኔ የጠላቶቼ መሳለቂያ፥ ለጐረቤቶቼ አስደንጋጭ፥ ለሚያውቁኝም አስፈሪ ነኝ፤ በመንገድ ሲያዩኝም ከእኔ ይሸሻሉ።


እንደ ሞተ ሰው ተረሳሁ፤ ተሰብሮ እንደ ተጣለ የሸክላ ዕቃ ሆንኩ።


ወዳጆቼና ጓደኞቼ ሕመሜን ተጸየፉ፤ ዘመዶቼም ከእኔ ራቁ፤


ሊገድሉኝ የሚፈልጉ ወጥመድ ይዘረጉብኛል፤ ሊጐዱኝ የሚያቅዱ ሊያጠፉኝ ይዝታሉ፤ በእኔም ላይ ቀኑን ሙሉ ያሤራሉ።


እንጀራዬን ከእኔ ጋር አብሮ የበላ ከልብ የምተማመንበት ወዳጄ እንኳ በእኔ ላይ በጠላትነት ተነሥቶአል።


ስድብ ልቤን ስለ ሰበረው ተስፋ ቈረጥኩ፤ የሚያስተዛዝነኝ ሰው ፈለግኹ፤ ነገር ግን ማንም አልነበረም፤ የሚያጽናናኝ ሰው ፈለግኹ፤ ነገር ግን ማንም አልተገኘም።


በወንድሞቼ መካከል እንግዳ፥ በእናቴም ልጆች መካከል ባይተዋር ሆንኩ።


ለቤትህ ያለኝ ቅናት በውስጤ እንደ እሳት ይነዳል፤ በአንተ ላይ የተሰነዘረው ስድብ በእኔ ላይ ዐረፈ።


የቅርብ ወዳጆቼንና ጓደኞቼን ከእኔ አርቀህ ጨለማ ብቻ ከእኔ ጋር እንዲቀር አደረግህ።


ወዳጆቼ ሁሉ ከእኔ እንዲርቁ አደረግህ፤ በፊታቸውም አጸያፊ አደረግኸኝ፤ ዙሪያዬ ታጥሮአል፤ ማምለጫም የለኝም።


“ጓደኞቼን ጠራሁ፤ እነርሱ ግን አታለሉኝ። ሕይወታቸውን ለማትረፍ ምግብ በመሻት ላይ ሳሉ ካህናቱና መሪዎቹ ሁሉ በከተማይቱ መንገዶች ሞቱ።


በሌሊት እጅግ ታለቅሳለች፤ እንባዋ በጒንጮችዋ ላይ ይወርዳል፤ ከአፍቃሪዎችዋ ሁሉ እርስዋን የሚያጽናና አንድ እንኳ የለም፤ ወዳጆችዋ የነበሩ ሁሉ ከድተዋታል፤ በጠላትነትም ተነሥተውባታል።


ነገር ግን ይህ ሁሉ የሆነው በነቢያት የተጻፈው እንዲፈጸም ነው።” በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ትተውት ሸሹ።


በተከሰስኩበት ነገር የመጀመሪያ መከላከያዬን ባቀረብኩ ጊዜ ሁሉም ተለዩኝ እንጂ ከእኔ ጋር ሆኖ የረዳኝ ማንም አልነበረም፤ ይህንንም ነገር እግዚአብሔር እንደ በደል አድርጎ አይቊጠርባቸው።


跟着我们:

广告


广告