Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 15:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 “የእግዚአብሔርን ሕልውና የሚክዱ ሰዎች ዘር አይወጣላቸውም፤ በጉቦ የተሠሩ ቤቶችም በእሳት ይጋያሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 የዐመፀኞች ጉባኤ ትመክናለች፤ የጉቦ ሱሰኞችም ድንኳን በእሳት ትበላለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 የአምላክ አልባ ሰው ጉባኤ ፍሬ የለውም፥ የጉቦ ድንኳኖችንም እሳት ትበላለች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ለኃ​ጥ​ኣን ሁሉ ሞት ምስ​ክ​ራ​ቸው ነው፥ እሳት የጉቦ ተቀ​ባ​ዮ​ችን ቤት ይበ​ላል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 የዝንጉዎች ጉባኤ ሁሉ ለጥፋት ይሆናል፥ የጉቦ ተቀባዮችንም ድንኳን እሳት ትበላለች።

参见章节 复制




ኢዮብ 15:34
17 交叉引用  

ኃጢአትን ከእጅህ ብታርቅ፥ ክፉ ነገርም በቤትህ እንዲገኝ ባታደርግ፥


ኀይላቸውን እንደ አምላክ አድርገው የሚቈጥሩ ሌቦችና እግዚአብሔርን የካዱ ሰዎች እንኳ በሰላም ይኖራሉ።


ከጨለማ ማምለጥ አይችልም፤ የእሳት ነበልባል ቅርንጫፎቹን እንዳደረቃቸውና አበባዎቹም በነፋስ እንደ ረገፉበት ዛፍ ይሆናል።


በቤቱ ውስጥ ምንም ነገር አይቀርለትም፤ በመኖሪያውም ውስጥ ዲን ይበተናል።


ናዕማታዊው ጾፋርም እንዲህ ሲል መለሰ፦


እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ከሥጋቸው በመለየት ዕድሜአቸውን ባሳጠረ ጊዜ፥ እግዚአብሔርን የሚክዱ ሰዎች ምን ተስፋ ይኖራቸዋል?


“በልባቸው እግዚአብሔርን የሚክዱ ዘወትር እንደ ተቈጡ ይኖራሉ፥ ሲቀጣቸው እንኳ ይቅርታ ለማግኘት አይጸልዩም።


እግዚአብሔርን የሚረሱ ሰዎች ሁሉ ፍጻሜአቸው ልክ እንደዚሁ ነው፤ እግዚአብሔር የለም የሚሉ ሰዎች ተስፋቸው ይቈረጣል።


የሚጠሉህ ሰዎች ግን የኀፍረት ሸማ ይከናነባሉ፤ የክፉ ሰዎችም ቤቶች ይጠፋሉ።”


ከምድሪቱ ላይ ታማኝ ሰው ጠፍቶአል፤ አንድም ትክክለኛ ሰው የለም፤ ሁላቸውም ሰውን ለመግደል ያደባሉ፤ እርስ በርሳቸውም አንዱ ሌላውን ተከታትሎ ያጠምዳል።


ያንን አገልጋይ ጌታው ይቀጣዋል፤ ዕጣ ክፍሉንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፤ በዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”


እነሆ አሁን በፊታችሁ ቆሜአለሁ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ንጉሥ ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወስጄአለሁ? የማንንስ አህያ ወስጄአለሁ? ማንንስ አታልዬአለሁ? ማንንስ ጨቊኜአለሁ? ፍርድን ለማዛባት ከማን ላይ ጉቦ ተቀብዬአለሁ? ከእነዚህ ሁሉ አንዱን አድርጌ ከሆነ የወሰድኩትን ለመመለስ ዝግጁ ነኝ።”


ነገር ግን የአባታቸውን መልካም አርአያነት አልተከተሉም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ የገንዘብ ጥቅም ፈላጊዎች ሆነው ጉቦ እየተቀበሉ ፍርድን ያጣምሙ ነበር።


跟着我们:

广告


广告