Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 15:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 የሽብርን ድምፅ በጆሮው ይሰማል፤ ሁሉ ነገር ሰላም መስሎ በሚታይበት ጊዜ አጥፊው ይመጣበታል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 የሚያስደነግጥ ድምፅ በጆሮው ላይ ይጮኻል፤ በሰላም ጊዜ ቀማኞች አደጋ ያደርሱበታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 የሚያስደነግጥ ድምፅ በጆሮው ነው፥ በሰላምም ሳለ ቀማኛ ይመጣበታል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግጥ ድም​ፅም በጆ​ሮው ነው፤ በደ​ኅ​ን​ነ​ትም ይኖር ዘንድ ተስፋ በሚ​ያ​ደ​ር​ግ​በት ጊዜ ጥፋት ይመ​ጣ​በ​ታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የሚያስደነግጥ ድምፅ በጆሮው ነው፥ በደኅንነቱም ሳለ ቀማኛ ይመጣበታል።

参见章节 复制




ኢዮብ 15:21
25 交叉引用  

ይህም የሆነበት ምክንያት እግዚአብሔር ሶርያውያንን በፈረሶችና በሠረገሎች የታጀበ የብዙ ሠራዊት ግሥጋሤ የሚመስል ድምፅ አሰምቶአቸው ስለ ነበር ነው፤ ይኸውም ሶርያውያን እንዳሰቡት የእስራኤል ንጉሥ የሒታውያንና የግብጽ ነገሥታትን ከነሠራዊቶቻቸው ቀጥሮ አደጋ ሊጥልባቸው የመጣ መስሎአቸው ነበር።


አስቴርም “ጠላታችንና ሞት የፈረደብንማ ሃማን የተባለው ይህ ክፉ ሰው ነው!” አለችው። ሃማንም እጅግ በመደንገጥ አንዴ ወደ ንጉሡ፥ አንዴ ወደ ንግሥቲቱ ይመለከት ነበር፤


የጨለማው ጊዜ አስፈራራው፤ አንድ ንጉሥ ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ዐይነት ሐዘንና ጭንቀት ይበረቱበታል።


“ፍርሀት በዙሪያው ከቦታል፤ በኋላው እየተከተለም ያሳድደዋል።


ያለ ስጋት ተማምኖ ከሚኖርበት ቤት ይባረራል፤ የሰው ሁሉ ገዢ ወደ ሆነው ወደ ሞት ይወሰዳል።


ሀብቱ ሁሉ ተሟጦ ስለሚያልቅ የሚቀምሰው ነገር አያገኝም።


በዚህም ምክንያት እነሆ፥ ዙሪያህን በወጥመድ ተከበሃል፤ ድንገተኛ አደጋም ያሸብርሃል፤


የጨለማ ሽብር ስለሚያስደስታቸው ለሁሉም ድቅድቅ ጨለማ ማለዳቸው ነው።”


ድንጋጤ እንደ ጐርፍ በድንገት ይደርስበታል፤ በሌሊትም ዐውሎ ነፋስ ይነጥቀዋል።


ክፉዎች እንደ ሣር ቶሎ ቢያድጉም፥ ክፉ አድራጊዎች ቢበለጽጉም፥ እነርሱ ለዘለዓለሙ ይጠፋሉ።


ደጋግ ሰዎች የሚፈልጉትን ያገኛሉ፤ ክፉዎች ግን እጅግ የፈሩት ነገር ይደርስባቸዋል።


ኃጢአተኞች ማንም ሳያሳድዳቸው ይሸሻሉ፤ ደግ ሰዎች ግን እንደ አንበሳ ደፋሮች ናቸው።


እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ይላል፦ “ሊያጠፋችሁ የመጣው ጠላት በድንገት አደጋ ሊጥልባችሁ ስለ ሆነ፥ ማቅ ለብሳችሁ በዐመድ ላይ ተንከባለሉ፤ አንድ ልጁ እንደ ሞተበት ሰው ምርር ብላችሁ አልቅሱ፤


“ከስደት የቀሩት ሁሉ ነፋስ የሚነካውን የቅጠል ኮሽታ በሰሙ ቊጥር በድንጋጤ በርግገው እንዲሸሹ አደርጋለሁ፤ በጦርነት ላይ ልክ ጠላት እንደሚያሳድዳቸው ያኽል ሆነው ይሸሻሉ፤ ምንም ዐይነት ጠላት በአጠገባቸው ሳይኖር ተደናቅፈው ይወድቃሉ፤


ከእነርሱ አንዳንዶቹ እንዳጒረመረሙና በቀሳፊው መልአክ እንደ ጠፉ እናንተም አታጒረምርሙ።


ሰዎች “ሁሉ ነገር ሰላምና የተረጋጋ ነው” ሲሉ እርጉዝ ሴትን ምጥ እንደሚይዛት ዐይነት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ በምንም ዐይነት አያመልጡም።


ንጉሥም ነበራቸው፤ እርሱ የጥልቁ ጒድጓድ መልአክ ነው፤ ስሙም በዕብራይስጥ አባዶን፥ በግሪክ አጶልዮን ይባላል፤


跟着我们:

广告


广告