Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 13:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ፊትህን ከእኔ ሰውረህ እንደ ጠላት የቈጠርከኝ ስለምንድን ነው?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ፊትህን ለምን ትሰውራለህ? እንደ ጠላትህስ ለምን ትቈጥረኛለህ?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ፊትህን ለምን ትሰውራለህ? እንደ ጠላትህም የቈጠርኸኝ ለምንድነው?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 “ፊት​ህን ከእኔ የሰ​ወ​ርህ፥ እንደ ጠላ​ት​ህም የቈ​ጠ​ር​ኸኝ ስለ​ምን ነው?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ፊትህን ከእኔ የሰወርህ፥ እንደ ጠላትህም የቈጠርኸኝ ስለ ምን ነው?

参见章节 复制




ኢዮብ 13:24
21 交叉引用  

ትዕቢት ቢሰማኝ እንደ አንበሳ አድነህ ትይዘኛለህ፤ እኔንም ለመጒዳት መላልሰህ ታደርጋለህ።


በእኔ ላይ የሚመሰክሩ ሰዎች ዘወትር ታገኛለህ፤ በእኔ ላይ የምታሳየው ቊጣ እያደገ ይሄዳል፤ እኔን ለማጥቃት ዘወትር አዳዲስ ዕቅዶችን እንደ ሠራዊት ታሰልፍብኛለህ።


እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦ በእኔ ላይ ያለህን ቅርታ ግለጥልኝ እንጂ አትፍረድብኝ!


እግዚአብሔር ተቈጥቶ ሰውነቴን ቈራረጠ፤ በጥላቻም ጥርሱን አፋጨብኝ፤ ጠላቴም ዐይኑን አፈጠጠብኝ።


እግዚአብሔር ተቈጥቶ መዓቱን አፈሰሰብኝ፤ እንደ ጠላትም ቈጠረኝ።


እግዚአብሔር እንዳሳደደኝ እናንተ ደግሞ ለምን ታሳድዱኛላችሁ? እስካሁንስ ያሠቃያችሁኝ አይበቃችሁምን?


እጅግ ጨከንክብኝ፤ በታላቅ ኀይልህም አሳደድከኝ።


“ምነው የሚሰማኝ ባገኘሁ! መከላከያዬን አቀርባለሁ፤ ሁሉን ቻይ አምላክ ይመልስልኝ! ምነው ከሳሼም የክሱን ዝርዝር በጽሑፍ አቅርቦልኝ ባየሁት!


ነገር ግን እግዚአብሔር እኔን ለመቅጣት ምክንያት ይፈልግብኛል እንደ ጠላትም ይቈጥረኛል፥


እግዚአብሔር ሆይ! ስለምን እንደዚህ ርቀህ ትቆማለህ? በችግር ጊዜስ ስለምን ትሰወራለህ?


እግዚአብሔር ሆይ፥ እስከ መቼ ትረሳኛለህ? የምትረሳኝ ለዘለዓለም ነውን? እስከ መቼስ ከእኔ ትሰወራለህ?


መጨቈናችንንና ችግራችንን ቸል በማለት ስለምን ከእኛ ትሰወራለህ?


መሬት እስክንነካ ድረስ አጐንብሰናል፤ በምድር ላይም ተዘርረናል።


እግዚአብሔር ሆይ! ለምን ትጥለኛለህ? ፊትህንስ ከእኔ ለምን ትሰውራለህ?


ምንም እንኳ እግዚአብሔር በእስራኤላውያን ላይ ፊቱን ቢመልስባቸውም እኔ በእርሱ ላይ እተማመናለሁ።


እግዚአብሔር እንደ ጠላት እስራኤልን አጠፋ፤ ቤተ መንግሥቶችዋን አወደመ፤ ምሽጎችዋን አፈራረሰ፤ በይሁዳ ሕዝብም ለቅሶና ዋይታን አበዛ።


‘ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ መጨረሻቸው ምን እንደሚሆን አያለሁ፤ እነርሱ የተበላሸ ትውልድ እምነት የሚጣልባቸው ልጆች አይደሉም’ አለ።


ሆኖም እንደ ወንድም ምከሩት እንጂ እንደ ጠላት አትቊጠሩት።


ሳሙኤልም ሳኦልን እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር ተለይቶህ ጠላትህ ከሆነ በኋላ እኔን ስለምን ታስጠራኛለህ?


跟着我们:

广告


广告