Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 12:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እግዚአብሔር ግን ጥበብና ኀይል አለው፤ ምክርና አስተዋይነት የሚገኙት ከእርሱ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “ጥበብና ኀይል የእግዚአብሔር ናቸው፤ ምክርና ማስተዋልም በርሱ ዘንድ ይገኛሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 “በእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ኃይል አለ፥ በእርሱ ዘንድ ምክርና ማስተዋል አለ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ጥበ​ብና ኀይል አለ፤ ለእ​ርሱ ምክ​ርና ማስ​ተ​ዋል አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ኃይል አለ፥ ለእርሱ ምክርና ማስተዋል አለው።

参见章节 复制




ኢዮብ 12:13
23 交叉引用  

የጥበብ መንገድ ብዙ ስለ ሆነ፥ ምነው ጌታ የጥበብን ምሥጢር ቢገልጥልህ! ስለዚህ እግዚአብሔር የቀጣህ፥ ከሚገባህ አሳንሶ መሆኑን ዕወቅ።


እግዚአብሔር ብርቱና ድል አድራጊ ነው፤ የሚታለልም ሆነ የሚያታልል ሁለቱም በእርሱ ሥልጣን ሥር ናቸው።


በኀይሉ ባሕርን ጸጥ ያደርጋል፤ በጥበቡም ረዓብ የተባለውን ታላቅ አውሬ ያጠፋል።


“በእርግጥ እግዚአብሔር ኀያል ነው፤ ማንንም አይንቅም፤ እርሱም ሁሉንም ነገር ያስተውላል።


ለልብ ጥበብን ለአእምሮስ ማስተዋልን የሰጠ ማነው?


እግዚአብሔር ጠቢብና ኀያል ነው፤ ማነው እርሱን ተቋቊሞ ያልተሸነፈ?


አምላካችን ታላቅና ኀያል ነው፤ ለዕውቀቱም ወሰን የለውም።


ምክርና መልካም ጥበብ ከእኔ ይገኛሉ፤ ማስተዋልና ብርታትም የእኔ ናቸው።


ሆኖም እግዚአብሔር ጥበበኛ ነው፤ መቅሠፍትንም ያመጣል፤ ቃሉን አያጥፍም፤ በክፉ ሰዎች ቤት ላይና ክፉዎችን በሚረዱ ሰዎች ላይ ይነሣል።


በመጨረሻ የሚሆነውን ነገር ከመጀመሪያው ጀምሬ ተናግሬአለሁ፤ ወደፊት ምን እንደሚሆን ከጥንት ጀምሬ ገልጬአለሁ፤ ዓላማዬ የጸና ይሆናል፤ የምፈቅደውንም አደርጋለሁ።


እግዚአብሔር በኀይሉ ምድርን ሠራ፤ በጥበቡም ዓለምን ፈጠረ፤ በማስተዋሉም ሰማያትን ዘረጋ፤


“ጥበብም ኀይልም የእርሱ ስለ ሆነ እግዚአብሔር ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን!


ከጠላቶቻችሁ ማንም ሊቋቋመው ወይም ሊቃወመው የማይችለውን አንደበትና ጥበብ እኔ እሰጣችኋለሁ።


“የጌታን አሳብ የሚያውቅ ማነው? የእርሱ አማካሪ የሚሆንስ ማነው?


ለተጠሩት ግን ለአይሁድም ሆነ ለግሪክ ሰዎች፥ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ኀይልና የእግዚአብሔር ጥበብ ነው።


ሁሉን ነገር በራሱ ፈቃድ የሚሠራ እግዚአብሔር አስቀድሞ በዐቀደልን መሠረት በክርስቶስ አማካይነት የእርሱ ወገኖች እንድንሆን መረጠን።


ጸጋውንም በጥበብና በዕውቀት ሁሉ አብዝቶ አፈሰሰልን።


የጥበብና የዕውቀት ሀብት ተሰውሮ የሚገኘው በክርስቶስ ዘንድ ነው።


ከእናንተ መካከል ጥበብ የጐደለው ሰው ቢኖር እግዚአብሔርን ይለምን፤ እግዚአብሔርም ይሰጠዋል፤ እርሱ ምንም ቅር ሳይለው ለሁሉም በልግሥና የሚሰጥ ቸር አምላክ ነው።


跟着我们:

广告


广告