Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 10:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 የምሄድበት ስፍራ የጨለማ ጥላና ሁከት የተሞላበት ምድር ነው፤ በዚያም ያለው ብርሃን እንደ ጨለማ ነው።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ብርሃኑ እንደ ጨለማ ወደ ሆነበት፣ የሞት ጥላ ወዳረበበበት፣ ሥርዐት የለሽ ወደ ሆነ ምድር፣ ድቅድቅ ጨለማ ወደ ሰፈነበት አገር ሳልሄድ ተወኝ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እንደ ጨለማም ወደ ጨለመች፥ ሥርዓትም ወደሌለባት ወደ ሞት ጥላ፥ ብርሃንዋም እንደ ጨለማ ወደ ሆነ ምድር ሳልሄድ፥ ጥቂት እጽናና ዘንድ ተወኝ፥ ልቀቀኝም።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 የዘ​ለ​ዓ​ለም ጨለ​ማም ወደ አለ​ባት፥ ብር​ሃ​ንም ወደ​ሌ​ለ​ባት፥ ማንም የሟ​ችን ሕይ​ወት ወደ​ማ​ያ​ይ​ባት ምድር ሳል​ሄድ ጥቂት አርፍ ዘንድ ተወኝ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እንደ ጨለማም ወደ ጨለመች፥ ሥርዓትም ወደሌለባት ወደ ሞት ጥላ፥ ብርሃንዋም እንደ ጨለማ ወደ ሆነ ምድር ሳልሄድ፥ ጥቂት እጽናና ዘንድ ተወኝ፥ ልቀቀኝም።

参见章节 复制




ኢዮብ 10:22
15 交叉引用  

ይኸውም ዳግመኛ ወደማልመለስበት ጭፍግግ ወዳለውና ድቅድቅ ጨለማ ወደ ሆነው አገር ከመሄዴ በፊት ነው።


ናዕማታዊውም ጾፋር እንዲህ አለ፦


ከእንግዲህ ወዲህ የሚኖረኝ ዕድል ፈንታ ወደ ሙታን ዓለም መውረድ ነው፤ እዚያም በጨለማ አልጋዬን እዘረጋለሁ።


አሁን በሰላም በተጋደምኩ፥ አንቀላፍቼም ዕረፍት ባገኘሁ ነበር።


በጭጋግና በድቅድቅ ጨለማ የተሸፈነ ይሁን፤ ደመና ረቦበት ጨለማ ብርሃኑን ይዋጠው፤


ክፉ አድራጊዎች የሚደበቁበት፤ ድቅድቅ ጨለማ ከቶ የለም።


የሞትን በሮች እንድታይ ተደርገሃልን? የድቅድቅ ጨለማንስ መዝጊያ አይተሃልን?


በጣም ጨለማ በሆነ ሸለቆ በኩል ባልሄድም እንኳ አንተ ከእኔ ጋራ ስለ ሆንክ፥ ምንም ክፉ ነገር አልፈራም። ያንተ በትርና ምርኲዝ ያጽናኑኛል።


ነገር ግን አራዊት በሚኖሩበት ስፍራ ሰብረኸናል። በድቅድቅ ጨለማም ሸፍነኸናል።


ተአምራትህ በጨለማ ስፍራ ይታወቃሉን? ታዳጊነትህስ በተረሱ ሰዎች አገር ይታያልን?


እግዚአብሔር ሆይ! እንድትረዳኝ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ በየማለዳውም ወደ አንተ እጸልያለሁ።


ባለህ ኀይል ሥራህን ሁሉ በትጋት ፈጽም፤ ወደ ሙታን ዓለም ከወረድህ በኋላ በዚያ ሥራና ሐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ የለም።


ጨለማን አምጥቶ በተራራዎች ከመሰናከላችሁ በፊት ተስፋ ያደረጋችኹትን ብርሃን ወደ ድቅድቅ ጨለማና ወደ ጥልቅ ጭጋግ ከመለወጡ በፊት አምላካችሁን እግዚአብሔርን አክብሩ።


እኔ እነርሱን ከምድረ ግብጽ አወጣኋቸው፤ በምድረ በዳ መራኋቸው፤ ጐድጓዳማ በሆነ መንገድ ድርቅና ጨለማ በበዛበት በረሓ፥ ማንም በማይኖርበትና በማይመላለስበት ምድር አሳለፍኳቸው፤ እነርሱ ግን ‘ይህን ሁሉ ያደረገልን አምላክ ወዴት ነው?’ ብለው እንኳ አልጠየቁም።


ከዚህም ሁሉ በላይ በእኛና በእናንተ መካከል ትልቅ ገደል አለ፤ ስለዚህ ከእኛ ወደ እናንተ፥ ከእናንተም ወደ እኛ መሻገር የሚችል ማንም የለም።’


跟着我们:

广告


广告