ኤርምያስ 8:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ስለዚህ እርሻቸውን ሁሉ ለሌሎች ርስት አድርጌ እሰጣለሁ፤ ሚስቶቻቸውንም ሌሎች ወንዶች እንዲቀሙአቸው አደርጋለሁ፤ ታላላቆችም ሆኑ ታናናሾች እያንዳንዱ ሰው በማታለል ጥቅምን ያግበሰብሳል፤ ነቢያትና ካህናት ሳይቀሩ ሕዝቡን ያታልላሉ፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ስለዚህ ሚስቶቻቸውንም ለሌሎች ወንዶች እሰጣለሁ፤ ዕርሻዎቻቸውንም ለባዕዳን እሰጣለሁ፤ ከታናሹ እስከ ታላቁ ድረስ፣ ሁሉም ተገቢ ላልሆነ ጥቅም ይስገበገባሉ፤ ነቢያትና ካህናትም እንዲሁ፤ ሁሉም ያጭበረብራሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉም በግፍ ለሚገኝ ጥቅም ስስታም ነውና፥ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም በተንኰል ያደርጋሉና ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች፥ እርሻቸውንም ለሚወርሱባቸው እሰጣለሁ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ስስትን ያስባሉና፥ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉ በተንኰል ያደርጋሉና ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች፥ እርሻቸውንም ለሚወርሱባቸው እሰጣለሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ስስትን ያስባሉና፥ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉ በተንኰል ያደርጋሉና ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች፥ እርሻቸውንም ለሚወርሱባቸው እሰጣለሁ። 参见章节 |