Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 7:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ይልቅስ በኢየሩሳሌም መንገዶችና በይሁዳ ከተሞች የሚያደርጉትን ሁሉ አትመለከትምን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እነርሱ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ላይ የሚያደርጉትን አታይምን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እነርሱስ በይሁዳ ከተሞች ውስጥና በኢየሩሳሌም አደባባይ ላይ የሚያደርጉትን አታይምን?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እነ​ር​ሱስ በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ውስ​ጥና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መን​ገ​ዶች የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን አታ​ይ​ምን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እነርሱስ በይሁዳ ከተሞች ውስጥና በኢየሩሳሌም አደባባይ ላይ የሚያደርጉትን አታይምን?

参见章节 复制




ኤርምያስ 7:17
11 交叉引用  

ሕዝቤ ኃጢአት ስለ ሠሩ እቀጣቸዋለሁ፤ እነርሱ እኔን ትተው ለሌሎች አማልክት ዕጣን ያጥናሉ፤ ምስሎችንም ሠርተው ይሰግዱላቸዋል።


ይህችን ከተማ የከበቡ ባቢሎናውያን መጥተው ያቃጥሉአታል፤ እንደዚሁም እኔን ለማስቈጣት በጣራዎቻቸው ላይ ለባዓል ጣዖት ዕጣን ያጥኑባቸው የነበሩትንና ለሌሎችም ጣዖቶች የመጠጥ መሥዋዕት ያቀርቡባቸው የነበሩትን ቤቶች ያቃጥላሉ።


የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ፥ የእነርሱ ነገሥታት፥ ባለሥልጣኖቻቸው፥ የእነርሱ ካህናትና ነቢያት በሚያደርጉአቸው ክፉ ነገሮች ሁሉ ቊጣዬን አነሣሥተዋል።


እኛ እንፈጽማለን ብለን ያሰብነውን ነገር ሁሉ እናደርጋለን፤ የሰማይ ንግሥት ተብላ ለምትጠራው አምላካችን ዕጣን እናጥናለን፤ እኛና የቀድሞ አባቶቻችን፥ ንጉሦቻችንና መሪዎቻችን በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ስናደርግ በነበረው ዐይነት አሁንም የወይን ጠጅ መባ እናቀርብላታለን። ይህን ሁሉ በምናደርግበት በዚያን ጊዜ ብዙ ሲሳይ ነበረን፤ ባለጸጎችም ስለ ነበርን ምንም ችግር አልነበረብንም።


እኔ የምጠላቸውን እነዚህን አጸያፊ ነገሮች እንዳታደርጉ ያስጠነቅቋችሁ ዘንድ አገልጋዮቼን ነቢያትን ወደ እናንተ ደጋግሜ ልኬ ነበር።


ስለዚህም በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ላይ ቊጣዬንና መዓቴን በማፍሰስ በእሳት እንዲጋዩ አደረግሁ፤ እነርሱም ዛሬ እንደሚታዩት ሁሉ ፍርስራሾችና ባድማ ሆነዋል።


ኤርምያስ ሆይ! ብረት እንደሚፈተን ሕዝቤን ፈትነህ ምን ዐይነት እንደ ሆኑ ዕወቅ፤


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ኤርምያስ ሆይ! ስለ ነዚህ ሕዝብ አትጸልይ፤ ስለ እነርሱ በመጸለይም አትጩኽ፤ ስለማልማለድህ ስለ እነርሱ ልትማልደኝ አያስፈልግም፤


ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፤ አባቶች እሳት ያቀጣጥላሉ፤ ሴቶች ‘የሰማይ ንግሥት’ ለተባለችው ጣዖት ኅብስት ለመጋገር ሊጥ ያቦካሉ፤ እኔንም ለማስቈጣት ለሌሎች አማልክት የወይን ጠጅ መባ ያቀርባሉ።


跟着我们:

广告


广告