Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 52:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 የይሁዳ ንጉሥ ኢኮንያን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት በዐሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያ አምስተኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ኤዌል መሮዳክ በነገሠበት ዓመት የይሁዳን ንጉሥ ኢኮንያንን ከእስር ፈታው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት፣ ዮርማሮዴክ በባቢሎን ነገሠ፤ በዚሁ ዓመት፣ በዐሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያ ዐምስተኛው ቀን የይሁዳን ንጉሥ ዮአኪንን ዐሰበው፤ ከእስር ቤትም አወጣው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 እንዲህም ሆነ፤ የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት በዓሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሀያ አምስተኛው ቀን፥ የባቢሎን ንጉሥ ኤዌል ማሮዴክ በነገሠ በአንደኛው ዓመት ለይሁዳ ንጉሥ ለዮአኪን ቸርነት አደረገለት ከእስር ቤትም አወጣው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢኮ​ን​ያን በተ​ማ​ረከ በሠ​ላሳ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት፥ በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በሃያ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን፥ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ዮር​ማ​ሮ​ዴቅ በነ​ገሠ በአ​ን​ደ​ኛው ዓመት የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የኢ​ኮ​ን​ያ​ንን ራስ ከፍ ከፍ አደ​ረገ፤ ከወ​ህ​ኒም አወ​ጣው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 እንዲህም ሆነ፥ የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት በአሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሀያ አምስተኛው ቀን፥ የባቢሎን ንጉሥ ዮርማሮዴክ በነገሠ በአንደኛው ዓመት የይሁዳን ንጉሥ የዮአኪንን ራስ ከፍ ከፍ አደረገ ከወህኒም አወጣው፥

参见章节 复制




ኤርምያስ 52:31
8 交叉引用  

በሦስት ቀን ጊዜ ውስጥ ንጉሡ ከእስራት ይፈታሃል፤ በደልህንም ይቅር ብሎ ወደ ቀድሞው ማዕርግህ ይመልስሃል፤ ቀድሞ የመጠጥ ቤት ኀላፊ ሆነህ ታደርገው እንደ ነበር የፈርዖንን ጽዋ በእጁ ትሰጠዋለህ።


በሦስተኛው ቀን የፈርዖን ልደት በዓል ስለ ነበረ ለመኳንንቱ ሁሉ ግብዣ አደረገ፤ በዚያኑ ቀን የወይን ጠጅ አሳላፊውና የእንጀራ ቤት ኀላፊው ከእስር ቤት ወጥተው በመኳንንቱ ፊት እንዲቀርቡ አደረገ።


እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ያዋርዳል፤ ትሑታንን ግን ያድናቸዋል።


አሁን ግን በከበቡኝ ጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ አደረግሁ፤ በደስታ “እልል” እያልኩ በመቅደሱ ውስጥ መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ እየዘመርኩም እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።


እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን ጋሻዬ ነህ፤ ድልን በማጐናጸፍ ክብርን የምትሰጠኝ አንተ ነህ።


የንጉሥ ልብ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ እርሱንም እንደ ወራጅ ውሃ ወደ ፈቀደው ይመራዋል። የንጉሥንም አእምሮ ይቈጣጠራል።


የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የኢዮስያስን ልጅ ሴዴቅያስን የኢዮአቄም ልጅ በነበረው በኢኮንያን ምትክ በይሁዳ ላይ አነገሠው።


跟着我们:

广告


广告