Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 49:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 አንድ መልእክት ከእግዚአብሔር ሰምቼአለሁ፤ “በኤዶም ሕዝብ ላይ አደጋ ለመጣል ተሰብሰቡ! ለጦርነትም ተነሡ!” ብሎ የሚናገር መልእክተኛ ወደ ሕዝቦች ተልኮአል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከእግዚአብሔር ዘንድ መልእክት ሰምቻለሁ፤ “እርሷን ለመውጋት ተሰብሰቡ፤ ለጦርነትም ውጡ” የሚል መልእክተኛ ወደ አሕዛብ ተልኳል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ከጌታ ዘንድ መልእክት ሰምቻለሁ በአሕዛብም መካከል፦ “ተሰብሰቡ፥ በእርሷም ላይ ኑ ለጦርነትም ተነሡ” የሚል መልእክተኛ ተልኮአል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 “ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ መስ​ማ​ትን ሰም​ቻ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛብ ሀገ​ሮች ተሰ​ብ​ሰቡ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ላይ ኑ፤ እር​ስ​ዋ​ንም ውጓት፥ የሚል መል​እ​ክ​ተኛ ተል​ኳል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ከእግዚአብሔር ዘንድ ወሬ ሰምቻለሁ በአሕዛብም መካከል፦ ተሰብሰቡ፥ በእርስዋም ላይ ኑ ለሰልፍም ተነሡ የሚል መልእክተኛ ተልኮአል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 49:14
12 交叉引用  

መልእክተኞቻቸው ዶአንና ሐኔስ ወደሚባሉት የግብጽ ከተሞች ደርሰዋል።


በሀገሩ ስላለ ጉዳይ በሹክሹክታ ወሬ እንዲሸበርና ወደ ሀገሩ ተመልሶ በሰይፍ እንዲገደል አደርገዋለሁ።”


“አሁን እንግዲህ በመንግሥታት መካከል ታናሽ፥ በሰዎችም መካከል የተናቅሽ አደርግሻለሁ።


የእግዚአብሔር ዓላማ ስለ ቤተ መቅደሱ የበቀል ዕርምጃ ለመውሰድ ስለ ሆነ ባቢሎንን ለማጥፋት የሜዶንን ነገሥታት አነሣሥቶአል፤ ስለዚህ ፍላጻችሁን ሳሉ! ጋሻችሁንም አንሡ!


ከምትሰሙትም የጒምጒምታ ወሬ የተነሣ በመፍራት ወኔአችሁ አይቀዝቅዝ፤ በየዓመቱ ልዩ ልዩ የጒምጒምታ ወሬ ይነዛል፤ በምድሪቱ ላይ አንዱ ንጉሥ ሌላውን እንደሚወጋ የሚገልጥ የዐመፅ ጒምጒምታ ወሬ ይሰማል።


የጦርነትን ድምፅና የጦርነትን ወሬ ትሰማላችሁ፤ ይህ ሁሉ መሆን ስላለበት አትደንግጡ፤ መጨረሻው ግን ገና ነው።


跟着我们:

广告


广告