ኤርምያስ 48:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 ለያዕዜር ሕዝብ ከማለቅሰው ይበልጥ ለሲብማ ሕዝብ እየጮኽኩ አለቅሳለሁ፤ የሲብማ ከተማ ሆይ! እንቺ ቅርንጫፎችዋ ሙት ባሕርን አልፎ እስከ ያዜር እንደሚደርስ የወይን ተክል ነሽ፤ ነገር ግን በጐመራው ፍሬሽና በወይን ዘለላሽ ላይ አጥፊው መጥቷል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም32 የሴባማ ወይን ሆይ፤ ለኢያዜር ካለቀስሁት እንኳ ይልቅ አለቅስልሻለሁ፤ ቅርንጫፎችሽ እስከ ባሕሩ ተዘርግተዋል፤ እስከ ኢያዜርም ደርሰዋል፤ ለመከር በደረሰው ፍሬሽና በወይንሽ ላይ፣ አጥፊው መጥቷል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 አንቺ የሴባማ ወይን ሆይ! ከኢያዜር ልቅሶ ይልቅ ለአንቺ አለቅሳለሁ፤ ቅርንጫፎችሽ ባሕርን ተሻግረዋል፥ ወደ ኢያዜርም ባሕር ደርሰዋል፤ አጥፊው በበጋ ፍሬሽና በወይንሽ ላይ መጥቷል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)32 አንቺ የሴባማ ወይን ሆይ! የኢያዜርን ልቅሶ ለአንቺ አለቅሳለሁ፤ ቅርንጫፎችሽ ባሕርን ተሻግረዋል፤ ወደ ኢያዜርም ባሕር ደርሰዋል፤ ሳይበስል በሰብልሽና በወይንሽ ላይ ጥፋት መጥቶአል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)32 አንቺ የሴባማ ወይን ሆይ፥ ከኢያዜር ልቅሶ ይልቅ ለአንቺ አለቅሳለሁ፥ ቅርንጫፎችሽ ባሕርን ተሻግረዋል፥ ወደ ኢያዜርም ባሕር ደርሰዋል፥ አጥፊው በሰብልሽና በወይንሽ ላይ መጥቶአል። 参见章节 |