Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 44:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “እናንተና የቀድሞ አባቶቻችሁ፥ ንጉሦቻችሁና መሪዎቻችሁ፥ በምድሪቱም የሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ፥ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ዕጣን ታጥኑ እንደ ነበረ፥ እግዚአብሔር አያስበውም ወይም ረስቶታል ብላችሁ ታስባላችሁን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 “እናንተና አባቶቻችሁ፣ ነገሥታታችሁና ባለሥልጣኖቻችሁ እንዲሁም የምድሪቱ ሕዝብ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ያጠናችሁትን እግዚአብሔር የማያስታውሰውና የዘነጋው ይመስላችኋልን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 “እናንተና አባቶቻችሁ ነገሥታቶቻችሁም አለቆቻችሁም የምድሪቱም ሕዝብ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ ያጠናችሁትን ዕጣን ጌታ አያስታውሰውምን? በልቡስ አያኖረውምን?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 “እና​ን​ተና አባ​ቶ​ቻ​ችሁ፥ ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ች​ሁም፥ አለ​ቆ​ቻ​ች​ሁም የም​ድ​ርም ሕዝብ በይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ ያጠ​ና​ች​ሁ​ትን ዕጣን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሰ​በው፥ በል​ቡም ያኖ​ረው አይ​ደ​ለ​ምን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እናንተና አባቶቻችሁ ነገሥታቶቻችሁም አለቆቻችሁም የምድርም ሕዝብ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ ያጠናችሁትን ዕጣን እግዚአብሔር ያሰበው በልቡም ያኖረው አይደለምን?

参见章节 复制




ኤርምያስ 44:21
19 交叉引用  

እርስዋም ኤልያስን “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ስለምን ይህን አደረግህብኝ? ወደዚህ የመጣኸው ኃጢአቴን አስታውሰህ ልጄ እንዲሞትብኝ ለማድረግ ነውን?” ስትል ጠየቀችው።


እኛ በጣም ስለ ተዋረድን በአባቶቻችን ኃጢአት ምክንያት አትቅጣን ፈጥነህም ምሕረት አድርግልን።


አምላክ ሆይ! አምርረህ አትቈጣ፤ ኃጢአታችንንም ለዘለዓለም አታስብብን፤ እኛ ሁላችን ሕዝብህ መሆናችንን አስታውስ።


የይሁዳ ሕዝብ ሆይ፥ በከተሞቻችሁ ልክ ብዙ አማልክት አሉአችሁ፤ በኢየሩሳሌምም መንገዶች ልክ አጸያፊ ለሆነው በዓል ተብሎ ለሚጠራው ባዕድ አምላክ መሥዋዕት የምታቀርቡበት ብዙ መሠዊያዎችን ሠርታችኋል።


እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ “ከእኔ ርቀው መሄድ ይወዳሉ፤ ራሳቸውንም አይቈጣጠሩም፤ ስለዚህ እኔ በእነርሱ ደስ አልሰኝም፤ የፈጸሙትን በደል ሁሉ በማስታወስ ስለ ኃጢአታቸው እቀጣቸዋለሁ።”


የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ፥ የእነርሱ ነገሥታት፥ ባለሥልጣኖቻቸው፥ የእነርሱ ካህናትና ነቢያት በሚያደርጉአቸው ክፉ ነገሮች ሁሉ ቊጣዬን አነሣሥተዋል።


እኛ እንፈጽማለን ብለን ያሰብነውን ነገር ሁሉ እናደርጋለን፤ የሰማይ ንግሥት ተብላ ለምትጠራው አምላካችን ዕጣን እናጥናለን፤ እኛና የቀድሞ አባቶቻችን፥ ንጉሦቻችንና መሪዎቻችን በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ስናደርግ በነበረው ዐይነት አሁንም የወይን ጠጅ መባ እናቀርብላታለን። ይህን ሁሉ በምናደርግበት በዚያን ጊዜ ብዙ ሲሳይ ነበረን፤ ባለጸጎችም ስለ ነበርን ምንም ችግር አልነበረብንም።


በዚህ ዐይነት የመለሱልኝን ወንዶች፥ ሴቶችና ሕዝብ ሁሉ እንዲህ አልኳቸው፦


በቀድሞ አባቶቻችሁ፥ በይሁዳ ነገሥታትና በሚስቶቻቸው፥ በእናንተ በራሳችሁና በሚስቶቻችሁ አማካይነት በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ላይ የተፈጸመውን ክፉ ሥራ ሁሉ ረስታችሁታልን?


መድረክ እየሠራሽ በየ አደባባዩ ለራስሽ ከፍ ያለ ቦታ አዘጋጀሽ።


ነገር ግን እኔ ይህን ሁሉ ክፋታቸውን እንደማስታውስ ከቶ አይገነዘቡም፤ ከዚህ የተነሣ በገዛ ኃጢአታቸው ተከበዋል፤ ክፉ ሥራቸው ሁሉ ከእኔ የተሰወረ አይደለም።”


ለያዕቆብና ለዘሮቹ መመኪያ የሆነው እግዚአብሔር እንዲህ ሲል በራሱ ማለ፦ “እነርሱ የሠሩትን ሥራ ሁሉ አልረሳም።


“ሴቶችና ወንዶች ልጆቻቸው ስላስቈጡት እግዚአብሔር አስወገዳቸው።


“ጠላቶቻችን የፈጸሙት በደል በእግዚአብሔር መዝገብ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል።


ታላቂቱ ከተማ ከሦስት ተከፈለች፤ የአሕዛብ ከተሞችም ፈራረሱ፤ እግዚአብሔር ታላቂቱን ባቢሎንን አስታወሰ፤ የብርቱ ቊጣው ወይን ጠጅ የተሞላበትን ጽዋ እንድትጠጣም አደረጋት።


የኃጢአትዋ ክምር እስከ ሰማይ ደርሶአል፤ እግዚአብሔር በደሎችዋን አስታውሶአል፤


ሄደህ በዐማሌቃውያን ላይ አደጋ በመጣል ያላቸውን ሁሉ ደምስስ፤ ከእነርሱ ምንም ነገር አታስቀር፤ ወንዶችን፥ ሴቶችን፥ ልጆችንና ሕፃናትን፥ ከብቶችን፥ በጎችን፥ ግመሎችንና አህዮችን ሁሉ ግደል።”


跟着我们:

广告


广告