Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 43:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ከዚህም በኋላ ዮሐናንና የሠራዊት አለቆች በይሁዳ የተረፉትን በሙሉ ወደ ግብጽ ወሰዱ፤ ይኸውም ከዚህ በፊት በአሕዛብ መካከል ተበታትነው ከቈዩ በኋላ እንደገና ወደ ይሁዳ አገር ተመልሰው የነበሩትን ሕዝብ ማለትም፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ነገር ግን፣ የቃሬያ ልጅ ዮሐናንና የጦር መኰንኖቹ ሁሉ፣ በይሁዳ ምድር ለመቀመጥ ከተበተኑበት ከአሕዛብ ሁሉ መካከል የተመለሱትን የይሁዳን ቅሬታዎች ሁሉ ይዘው ሄዱ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የቃሬያም ልጅ ዮሐናን የጭፍራ አለቆችም ሁሉ በይሁዳ ምድር ለመቀመጥ ከተሰደዱባቸው ከአሕዛብ ስፍራዎች ሁሉ የተመለሱትን የይሁዳን ትሩፍ ሁሉ፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ የጭ​ፍራ አለ​ቆ​ችም ሁሉ በይ​ሁዳ ምድር ለመ​ቀ​መጥ ከተ​ሰ​ደ​ዱ​ባ​ቸው ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ የተ​መ​ለ​ሱ​ትን የይ​ሁ​ዳን ቅሬታ ሁሉ ወሰዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የቃሬያም ልጅ ዮሐናን የጭፍራ አለቆችም ሁሉ በይሁዳ ምድር ለመቀመጥ ከተሰደዱባቸው ከአሕዛብ ሁሉ የተመለሱትን የይሁዳን ቅሬታ ሁሉ፥

参见章节 复制




ኤርምያስ 43:5
7 交叉引用  

የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የሳፋን የልጅ ልጅ የአሒቃም ልጅ ገዳልያን ወደ ባቢሎን ተማርከው ሳይወሰዱ ለቀሩት ሰዎች ሁሉ ኀላፊ ይሆን ዘንድ የይሁዳ ገዢ አድርጎ ሾመው።


እኔም በዚህቹ በምጽጳ ከእናንተ ጋር ስለምኖር ባቢሎናውያን በሚመጡበት ጊዜ የእናንተ ወኪል ሆኜ እቆምላችኋለሁ፤ እናንተ ግን በምትኖሩባቸው መንደሮች ሁሉ የወይኑን ዘለላ፥ የወይራውን ዘይትና የሌላውን ተክል ፍሬ ሰብስባችሁ አከማቹ”


ከዚያም በኋላ የንጉሡን ሴቶች ልጆችና የቀሩትንም ሕዝብ በምጽጳ አሰረ፤ እነዚህም ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ ጦር አዛዥ ናቡዛርዳን በገዳልያ ሥር እንዲጠበቁ ዐደራ የተሰጡ ነበሩ፤ እስማኤል ግን እነዚህን ሁሉ ማርኮ ወደ ዐሞን ግዛት አቅጣጫ ተሻገረ።


እነርሱም የባቢሎን ንጉሥ ገዢ አድርጎ የሾመውን ገዳልያንን እስማኤል ስለ ገደለው ባቢሎናውያን አደጋ ያደርሱብናል ብለው ፈርተው ነበር፤ ስለዚህም ከባቢሎናውያን ፊት ሸሽተው ወደ ግብጽ ለመኰብለል ተነሡ፤ በቤተልሔም አጠገብ ባለችው ጌሩት ኪምሀም ተብላ በምትጠራው ቦታ ዕረፍት አደረጉ።


ንጉሥ ሆይ! የምልህን አድምጠኝ! አንተን በእኔ ላይ ያነሣሣህ እግዚአብሔር ቢሆን ኖሮ፥ መሥዋዕት በማቅረብ ቊጣውን እንዲመልስ ማድረግ በተቻለ ነበር፤ ነገር ግን ይህን ያደረጉት ሰዎች ከሆኑ ሄደህ ባዕዳን አማልክትን አምልክ ብለው እግዚአብሔር ከሰጠኝ ርስት ድርሻ ስላባረሩኝ በእግዚአብሔር ፊት የተረገሙ ይሁኑ።


跟着我们:

广告


广告