Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 4:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እግዚአብሔር ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ “እዳሪውን መሬት እረሱ፤ ዘራችሁን በሾኽ መካከል አትዝሩ!

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እግዚአብሔር ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ሰዎች እንዲህ ይላል፤ “ዕዳሪውን መሬት ዕረሱ፤ በእሾኽም መካከል አትዝሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ጌታ ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ሰዎች እንዲህ ይላልና፦ “ያልታረሰ መሬታችሁን እረሱ በእሾህም ላይ አትዝሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለይ​ሁዳ ወን​ዶ​ችና ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነዋ​ሪ​ዎች እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ልባ​ች​ሁን አድሱ በእ​ሾ​ህም ላይ አት​ዝሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እግዚአብሔር ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ሰዎች እንዲህ ይላልና፦ ጥጋቱን እርሻ እረሱ በእሾህም ላይ አትዝሩ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 4:3
10 交叉引用  

ምድር እሾኽና አሜከላ ታበቅላለች፤ አንተም የዱር ተክሎችን ትበላለህ።


በሰባተኛው ዓመት ግን በሕዝብህ መካከል የሚገኙ ድኾች ምግብ ያገኙ ዘንድ በምድሪቱ ላይ ምንም ነገር አታምርት፤ ምድሪቱ ታርፍ ዘንድ ተዋት፤ ከእነርሱ የተረፈውንም የምድር አራዊት ይመገቡት፤ የወይን ተክል ቦታህንና የወይራ ዘይት ዛፎችህንም እንደዚሁ አሳርፋቸው።


እኔም ‘እንግዲህ ዕዳሪውን መሬት ዕረሱ፤ ጽድቅን ለራሳችሁ ዝሩ፤ የማይለዋወጥ ፍቅርን ሰብስቡ፤ እነሆ ወደ እኔ ወደ አምላካችሁ የምትመለሱበት ጊዜ አሁን ነው! እኔም መጥቼ ፍትሕን አሰፍንላችኋለሁ’ አልኩ።


በእሾኻማ ቊጥቋጦ መካከል የተዘራው የሚያመለክተው፥ ቃሉን ለጊዜው የሚሰማውን ሰው ነው፤ ይሁን እንጂ የዚህ ዓለም ሐሳብና የሀብት ፍቅር ወደ ልቡ ገብቶ ቃሉን ስለሚያንቀው ያለ ፍሬ ይቀራል።


ሌላውም ዘር በእሾኻማ ቊጥቋጦ መካከል ወደቀ፤ እሾኻማውም ቊጥቋጦ አደገና የዘሩን ቡቃያ አንቆ አስቀረው።


ሌላው ዘር በእሾኽ ቊጥቋጦ መካከል ወደቀ፤ እሾኹም ባደገ ጊዜ ስላነቀው ያለ ፍሬ ቀረ።


በእሾኽም ቊጥቋጦ መካከል የወደቀው ዘር የሚያመለክተው ቃሉን ለጊዜው የሚሰሙትን ሰዎች ነው፤ ነገር ግን የዚህ ዓለም ሐሳብና ሀብት፥ የምድራዊ ኑሮ ምቾትም አንቆ ያለ ፍሬ ያስቀራቸዋል።


ሌላውም ዘር በእሾኽ መካከል ወደቀ፤ እሾኹ አብሮ አደገና አንቆ አስቀረው።


跟着我们:

广告


广告