ኤርምያስ 38:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 ከዚያም በኋላ ባለ ሥልጣኖቹ መጥተው ጠየቁኝ፤ እኔም ልክ ንጉሡ ያለኝን ብቻ ነገርኳቸው፤ እኔና ንጉሡ ስንወያይ የሰማ ማንም ስላልነበረ ከዚያ በኋላ ጥያቄአቸውንም አቆሙ፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም27 መኳንንቱ ሁሉ ወደ ኤርምያስ መጥተው ጠየቁት፤ እርሱም ንጉሡ ያዘዘውን ቃል ሁሉ ነገራቸው፤ ከንጉሡ ጋራ የተነጋገሩትን ነገር የሰማ አንድም ሰው ስላልነበረ፣ ከዚህ በላይ አላነጋገሩትም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 አለቆቹም ሁሉ ወደ ኤርምያስ መጥተው ጠየቁት፥ እርሱም ንጉሡ እንዳዘዘው እነዚህን ሁሉ ቃላት ነገራቸው። ነገሩም አልተሰማም ነበርና ከእርሱ ጋር መነጋገርን ተዉ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 አለቆቹም ሁሉ ወደ ኤርምያስ መጥተው ጠየቁት፤ ንጉሡም እንዳዘዘው እንደዚህ ቃል ሁሉ ነገራቸው። ነገሩም አልተሰማምና ከእርሱ ጋር መነጋገርን ተዉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 አለቆቹም ሁሉ ወደ ኤርምያስ መጥተው ጠየቁ፥ ንጉሡም እንዳዘዘው እንደዚህ ቃል ሁሉ ነገራቸው። ነገሩም አልተሰማምና ከእርሱ ጋር መነጋገርን ተዉ። 参见章节 |