ኤርምያስ 34:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 እነሆ እኔ እግዚአብሔር እናንተንም የምላችሁ ይህ ነው፦ ‘አልታዘዛችሁም፤ ወገኖቻችሁ ለሆኑ እስራኤላውያንም ነጻነት አልሰጣችሁም፤’ ስለዚህም እኔ በጦርነት፥ በራብና በወረርሽኝ ትሞቱ ዘንድ እተዋችኋለሁ፤ በእናንተ ላይ በማደርገውም ነገር የዓለም ሕዝብ ሁሉ እንዲሠቀቅ አደርጋለሁ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም17 “ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ለወንድሞቻችሁና ለወገኖቻችሁ ነጻነት አላወጃችሁምና አልታዘዛችሁኝም። እንግዲህ እኔ ነጻነት ዐውጅላችኋለሁ፤’ ይላል እግዚአብሔር። ‘ይኸውም በሰይፍ፣ በቸነፈርና በራብ የምትወድቁበት ነጻነት ነው። ለምድር መንግሥታት ሁሉ መሠቀቂያ አደርጋችኋለሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 “ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሰው ሁሉ ለወንድሙና ለባልንጀራው የአርነት አዋጅ ለመንገር እኔን አልሰማችሁም፤ እነሆ፥ እኔ ለሰይፍና ለቸነፈር ለራብም የአርነት አዋጅ እናገርባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ በምድር መንግሥታትም ሁሉ ዘንድ ለድንጋጤ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሰው ሁሉ ለወንድሙና ለባልንጀራው ዓመተ ኅድገትን ለማድረግ እኔን አልሰማችሁም፤ እነሆ እኔ ለሰይፍና ለቸነፈር፥ ለራብም ዓመተ ኅድገትን አውጅባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ በምድርም መንግሥታት ሁሉ መካከል እበትናችኋለሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰው ሁሉ ለወንድሙና ለባልንጀራው የአርነት አዋጅ ለመንገር እኔን አልሰማችሁም፥ እነሆ፥ እኔ ለሰይፍና ለቸነፈር ለራብም የአርነት አዋጅ እናገርባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በምድርም መንግሥታት ሁሉ መካከል እንድትበተኑ አደርጋችኋለሁ። 参见章节 |