Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 3:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ምንም እንኳ እስራኤል ከእርሱ ብትለይ፥ እምነት ከማይጣልባት ከይሁዳ የምትሻልበት መንገድ መኖሩን እግዚአብሔር ነገረኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “ከከሓዲዋ ይሁዳ ይልቅ ከዳተኛዪቱ እስራኤል ጻድቅ ሆና ተገኘች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 “ጌታም እንዲህ አለኝ፦ ከአታላይቱ ከይሁዳ ይልቅ ከዳተኛይቱ እስራኤል ጸደቀች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ከጎ​ስ​ቋ​ላዋ ይሁዳ ይልቅ ከዳ​ተ​ኛ​ዪቱ እስ​ራ​ኤል ራስ​ዋን አጸ​ደ​ቀች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ከአታላይቱ ከይሁዳ ይልቅ ከዳተኛይቱ እስራኤል ጸደቀች።

参见章节 复制




ኤርምያስ 3:11
9 交叉引用  

እኔ ያዘዝኳቸውን ለመፈጸም እምቢ ይሉ እንደ ነበሩት እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው ኃጢአት ይሠራሉ፤ ባዕዳን አማልክትን ያመልካሉ፤ እስራኤልና ይሁዳ በአንድነት ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል።


እናንተ ከእግዚአብሔር ርቃችሁ የነበራችሁ ሁሉ ተመለሱ፤ እርሱ ይፈውሳችኋል፤ ታማኞችም ያደርጋችኋል። እናንተም እንዲህ ብላችኋል፦ “አዎ! እግዚአብሔር አምላካችን ስለ ሆነ ወደ እርሱ እንመለሳለን፤


ይህን ሁሉ ከፈጸመች በኋላ እንደገና ወደ እኔ የምትመለስ መስሎኝ ነበር፤ እርስዋ ግን አልተመለሰችም፤ እምነት የማይጣልባት የእርስዋ እኅት ይሁዳም ይህን ሁሉ አይታለች።


እስራኤል እኔን ማምለክዋን ትታ የጣዖት አምልኮን ተከተለች፤ ይህንንም ስታደርግ የተውኳት መሆኔን ይሁዳ ተመልክታለች፤ እምነት የማይጣልባት የእስራኤል እኅት ይሁዳ ፍርሀት አላደረባትም፤ እርስዋም በበኩልዋ ጣዖት አምላኪ ሆናለች።


የእነርሱን አካሄድ ተከትለሽ አጸያፊ ሥራቸውን መሥራትሽ ብቻ ሳይሆን በአካሄድሽ ሁሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከእነርሱ የበለጠ ጥፋት ሠራሽ።


“እኅትዋ ኦሆሊባ ይህንንም ካየች በኋላ ባሰባት እንጂ አልታረመችም፤ እንዲያውም ከኦሆላ የበለጠ አመንዝራ ሆነች።


ሕዝቤ ከእኔ መራቅን ፈለጉ፤ ይሁን እንጂ ለእርዳታ ወደ ላይ ይጮኻሉ፤ ግን ማንም ከችግራቸው አያወጣቸውም።


የእስራኤል ሕዝብ እንደ እልኸኛ ጊደር እምቢተኞች ሆነዋል፤ ታዲያ እግዚአብሔር እነርሱን እንደ በግ ጠቦቶች በመልካም መስክ እንዴት ያሰማራቸዋል?


跟着我们:

广告


广告