ኤርምያስ 29:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 ዕድል ፈንታቸውም ይህ የሚሆንበት ምክንያት አሠቃቂ ኃጢአት በመሥራታቸው ነው፤ ይኸውም ከባልንጀሮቻቸው ሚስቶች ጋር አመንዝረዋል፤ እኔም ያላዘዝኳቸውን የሐሰት ቃል በስሜ ተናግረዋል፤ ይህም እኔ ያልፈቀድኩት ነገር ነው፤ ያደረጉትን ሁሉ ስለማውቅባቸው በእነርሱ ላይ እመሰክርባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።’ ” 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም23 ከባልንጀሮቻቸው ሚስቶች ጋራ በማመንዘርና ያልነገርኋቸውን ቃል በስሜ በሐሰት በመናገር በእስራኤል ዘንድ በደል ፈጽመዋልና። ይህንም እኔ ዐውቃለሁ፤ ምስክር ነኝ” ይላል እግዚአብሔር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 በእስራኤል ዘንድ አሳፋሪ ነገር አድርገዋልና፤ ከባልንጀሮቻቸውም ሚስቶች ጋር አመንዝረዋልና፤ ያላዘዝኋቸውንም ቃል በስሜ በሐሰት ተናግረዋልና፤ እኔም አውቀዋለሁ ምስክርም ነኝ፥ ይላል ጌታ።’ ” 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 በእስራኤል ዘንድ ክፉ አድርገዋልና፥ ከባልንጀሮቻቸውም ሚስቶች ጋር አመንዝረዋልና፥ ያላዘዝኋቸውንም ቃል በስሜ በሐሰት ተናግረዋልና። እኔም አውቃለሁ፤ ምስክርም ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 በእስራኤል ዘንድ ስንፍና አድርገዋልና፥ ከባልንጀሮቻቸውም ሚስቶች ጋር አመንዝረዋልና፥ ያላዘዝኋቸውንም ቃል በስሜ በሐሰት ተናግረዋልና። 参见章节 |