ኤርምያስ 25:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 እግዚአብሔር በተከታታይ አገልጋዮቹን ነቢያቱን ቢልክላችሁም እናንተ ልብ ብላችሁ አላዳመጣችሁም፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም4 እግዚአብሔር አገልጋዮቹን ነቢያትን ሁሉ ደጋግሞ ወደ እናንተ ላከ፤ ሆኖም አልሰማችሁም፤ ትኵረትም አልሰጣችሁትም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ጌታም ማልዶ ተነሥቶ ባርያዎቹን ነቢያትን ሁሉ ወደ እናንተ ላከ፤ ልኮም ግን እናንተ አላደመጣችሁም፥ ለመስማትም ጆሮአችሁን አላዘነበላችሁም። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 እግዚአብሔርም ባሪያዎቹን ነቢያትን ወደ እናንተ ላከ፤ እነርሱም ማልደው ገሠገሡ፤ እናንተም አልሰማችኋቸውም፤ ለመስማትም ጆሮአችሁን አላዘነበላችሁም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 እግዚአብሔርም ማልዶ ተነሥቶ ባሪያዎቹን ነቢያትን ወደ እናንተ ላከ፥ እናንተም አላደመጣችሁም ጆሮአችሁንም አላዘነበላችሁም። 参见章节 |