Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 25:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ጽዋውን ከእጅህ ተቀብለው ለመጠጣት እምቢ የሚሉ ከሆነ፥ ‘ከዚህ ጽዋ መጠጣት እንዳለባችሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አዞአል’ ብለህ ንገራቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ነገር ግን ጽዋውን ከእጅህ ለመውሰድና ለመጠጣት እንቢ ካሉ፣ እንዲህ በላቸው፤ “የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በግድ ትጠጣላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ጽዋውንም ከእጅህ ተቀብለው ለመጠጣት እንቢ ቢሉ፦ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ፈጽማችሁ ትጠጣላችሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ይጠ​ጡም ዘንድ ጽዋ​ውን ከእ​ጅህ ለመ​ቀ​በል እንቢ ቢሉ፦ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ፈጽ​ማ​ችሁ ትጠ​ጣ​ላ​ችሁ” በላ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ይጠጡም ዘንድ ጽዋውን ከእጅህ ለመቀበል እንቢ ቢሉ፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ፈጽማችሁ ትጠጣላችሁ በላቸው።

参见章节 复制




ኤርምያስ 25:28
12 交叉引用  

ታዲያ፥ አንተ ንስሓ መግባት እንቢ እያልክ፥ አንተ በምታቀርበው ሐሳብ መሠረት እግዚአብሔር ምኞትህን እንዲፈጽምልህ ትፈልጋለህን?


ስለዚህ ጽዋውን ከእግዚአብሔር እጅ ወሰድኩና እግዚአብሔር ወደ ላከኝ ሕዝቦች ሁሉ ሄጄ እንዲጠጡት አደረግሁ፤


“ነገር ግን ማንኛውም ሕዝብ ወይም መንግሥት ‘እርሱን አላገለግልም፤ በቀንበሩም ሥር ሆኜ አልገዛም’ ቢል ናቡከደነፆር ራሱ እንዲደመስሰው እስከ ፈቀድኩለት ድረስ፥ በጦርነት፥ በራብና በወረርሽኝ እንዲቀጡ አደርጋለሁ።


ምድር ታለቅሳለች፤ ሰማይም በጨለማ ይጋረዳል፤ ይህን እግዚአብሔር ተናግሮአል፤ ሐሳቡም አይለወጥም፤ ቊርጥ ውሳኔ አድርጎአል፤ ወደ ኋላም አይመለስም።


“እንግዲህ መቀጣት የማይገባቸው ሰዎች እንኳ የቅጣቱን ጽዋ ገፈት የሚቀምሱ ከሆነ እናንተ ያለ ቅጣት የምታመልጡ ይመስላችኋልን? አይደለም፤ እናንተም ከቅጣቱ ጽዋ መጠጣት አለባችሁ።


ባቢሎንን ማንም የማይኖርባት ምድረ በዳ እንድትሆን ለማድረግ እግዚአብሔር ያቀደውን የሚፈጽምበት ጊዜ ከመሆኑ የተነሣ፥ ምድር በመናወጥ ትንቀጠቀጣለች።


በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ ዘንድ ኢምንት ናቸው፤ በሰማይ መላእክትም ሆነ በምድር በሚኖሩ ሕዝቦች ላይ የፈቀደውን ያደርጋል፤ ፈቃዱን እንዳያደርግ ሊከለክለው የሚችል ወይም ‘ምን እያደረግህ ነው’ የሚለው ማንም የለም።


ሕዝቤ በተቀደሰው ተራራዬ ላይ የመከራ ጽዋ ጠጥተዋል፤ በዙሪያው ያሉት አሕዛብ ሁሉ ከዚህ የከፋ የመከራ ጽዋ ይጠጣሉ፤ የጠጡትም ሁሉ እንዳልነበሩ ይሆናሉ።”


እንዲህም የሆነው አንተ አስቀድመህ በገዛ ኀይልህና በገዛ ፈቃድህ ያቀድከውን ለመፈጸም ነው፤


ሁሉን ነገር በራሱ ፈቃድ የሚሠራ እግዚአብሔር አስቀድሞ በዐቀደልን መሠረት በክርስቶስ አማካይነት የእርሱ ወገኖች እንድንሆን መረጠን።


跟着我们:

广告


广告