ኤርምያስ 2:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም36 ወደ ባዕዳን ሕዝብ አማልክት ዘወር በማለትሽ ራስሽን አቃለሻል፤ ከዚህ በፊት በአሦር ምክንያት ኀፍረት እንደ ደረሰብሽ አሁን ደግሞ በግብጽ ምክንያት ኀፍረት ይደርስብሻል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም36 መንገድሽን እየለዋወጥሽ፣ ለምን ትሮጫለሽ? አሦር እንዳዋረደሽ፣ ግብጽም እንዲሁ ያዋርድሻል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)36 መንገድሽን ለመለወጥ ለምን በጣም ትሮጫለሽ? አሦር እንዳሳፈረሽ ግብጽ እንዲሁ ያሳፍርሻል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)36 መንገድሽን እጥፍ ታደርጊ ዘንድ ለምን እጅግ ትሮጫለሽ? በአሦር እንዳፈርሽ በግብፅም ታፍሪያለሽ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)36 መንገድሽን ትለውጪ ዘንድ ለምን እጅግ ትሮጫለሽ? አሦር እንዳሳፈረሽ ግብጽ ያሳፍርሻል። 参见章节 |