Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 2:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 በበረሓ መኖርን የለመደች የሜዳ አህያ፥ ፍትወት በተቀሰቀሰባት ጊዜ ማን ሊቈጣጠራት ይችላል? ወንዶች የሜዳ አህዮች ያሉበትን ስፍራ፥ ራስዋ አነፍንፋ ስለምትደርስበት፥ እነርሱ እርስዋን በመፈለግ መድከም አያስፈልጋቸውም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 በምድረ በዳ እንደ ለመደች፣ በፍትወቷ ነፋስን እንደምታነፈንፍ፣ የሜዳ አህያ ነሽ፤ ከመጐምጀቷ ማን ሊገታት ይችላል? ለሚፈልጓት ሁሉ ያለ ምንም ድካም በፍትወቷ ወራት በቀላሉ ትገኝላቸዋለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 በምኞትዋ ነፋስን እንደምታሸትት፥ በምድረ በዳ እንደ ለመደች እንደ ሜዳ አህያ ነሽ፤ ከጋለው ምኞትዋ የሚመልሳት ማን ነው? የሚሹአት ሁሉ አይደክሙም፥ በወራትዋ ያገኙአታል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 በም​ድረ በዳ ባሉ ውኃ​ዎች ተዘ​ረ​ጋች፤ በሰ​ው​ነ​ቷም ምኞት ትወ​ሰ​ዳ​ለች፤ ይይ​ዟ​ታል፤ የሚ​መ​ል​ሳት ግን የለም፤ የሚ​ሹ​አ​ትም አይ​ደ​ክ​ሙም፤ በተ​ዋ​ረ​ደ​ች​በ​ትም ጊዜ ያገ​ኙ​አ​ታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 በምኞትዋ ነፋስን እንደምታሸትት፥ በምድረ በዳ እንደ ለመደች እንደ ሜዳ አህያ ነሽ፥ ከምኞትዋ የሚመልሳት ማን ነው? የሚሹአት ሁሉ አይደክሙም፥ በወራትዋ ያገኙአታል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 2:24
8 交叉引用  

ሞኝ ሰው ጥበበኛ ከሚሆን ይልቅ የሜዳ አህያ ሰው ሆኖ ቢወለድ ይቀላል።


በእርግዝና ምን ያኽል ጊዜ እንደምትቈይ፥ መቼስ እንደምትወልድ ታውቃለህን?


የሜዳ አህዮች ከውሃ ጥም የተነሣ፥ በየኰረብታው ጫፍ ላይ ቆመው እንደ ቀበሮ ያለከልካሉ፤ ምግብ ስለማያገኙም የማየት ኀይላቸው ይቀንሳል።


ዛፍን ‘አባታችን’፥ አለትንም ‘የወለድሽን እናታችን’ የምትሉ ሁሉ ኀፍረት ይደርስባችኋል፤ ይህም የሚሆነው ወደ እኔ በመመለስ ፈንታ ከእኔ ስለ ራቃችሁ ነው፤ መከራ ሲደርስባችሁ ግን መጥቼ እንዳድናችሁ ትጠይቁኛላችሁ።


አመንዝራ ሴት ገንዘብ ይከፈላት ነበር፤ አንቺ ግን ገንዘብ በመቀበል ፈንታ ለወዳጆችሽ ስጦታ ታበረክቺአለሽ፤ ከየአቅጣጫው መጥተው ከአንቺ ጋር ያመነዝሩ ዘንድ መደለያ ገንዘብ ሰጠሽ።


“መከራ ሲበዛባቸው እኔን ይፈልጋሉ፤ ስለዚህ የሠሩትን በደል ተገንዝበው ወደ እኔ እስከሚመለሱ፥ ድረስ ከእነርሱ እርቃለሁ።”


ብቻውን እንደሚንከራተት የምድረ በዳ አህያ ወደ አሦር ሄዱ፤ እንዲጠብቁአቸውም ዋጋ በመክፈል መንግሥታትን ተለማመጡ፤


跟着我们:

广告


广告