ኤርምያስ 2:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 ታዲያ ‘ራሴን ከቶ አላረክስም፤ ለበዓልም ከቶ አልሰግድም’ ብለሽ ለማስተባበል እንዴት ትችያለሽ? በሸለቆ ውስጥ ኃጢአት በመሥራት ያደረግሽውን ርኲሰት እስቲ ተመልከቺ፤ በፍትወት እንደ ተቃጠለች የበረሓ ግመል፥ ወዲያና ወዲህ ትባዝኚአለሽ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም23 “ ‘አልረከስሁም፣ በኣሊምን አልተከተልሁም’ እንዴት ትያለሽ? በሸለቆ ውስጥ ምን እንዳደረግሽ እስኪ አስቢ፣ ምንስ እንደ ፈጸምሽ ተገንዘቢ፤ እንደምትፋንን ፈጣን ግመል ሆነሻል፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 አንቺስ፦ ‘ራሴን አላረከስኩም በዓሊምንም አልተከተልኩም’ እንዴት ትያለሽ? በሸለቆ ያለውን መንገድሽን ተመልከቺ፥ ምን እንዳደረግሽም እወቂ፤ በመንገዶችዋ ላይ ወድያና ወዲህ የምትቅበዘበዥ ወጣት ግመል ሆነሻል፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 አንቺስ፦ አልረከስሁም፤ በዓሊምንም አልተከተልሁም፤ እንዴት ትያለሽ? በሸለቆ ያለውን መንገድሽን ተመልከቺ፤ ያደረግሽውንም ዕወቂ። ማታ ማታ በመንገዶች ትጮኻለች፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 አንቺስ፦ አልረከስሁም በአሊምንም አልተከተልሁም እንዴት ትያለሽ? በቈላ ያለውን መንገድሽን ተመልከቺ፥ ያደረግሽውንም እወቂ፥ በመንገድም ላይ እንደ ተለቀቀች እንደ ፈጣን ግመል ሆነሻል፥ 参见章节 |