ኤርምያስ 18:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 ታዲያ የደግ ሥራ ዋጋው ክፉ ነገር ማድረግ ነውን? አንተ በእነርሱ ላይ እንዳትቈጣ እኔ በፊትህ ቆሜ ስለ እነርሱ እንደማለድኩህ አስብ፤ እነርሱ ግን እነሆ እኔ የምወድቅበትን ጒድጓድ ቈፈሩ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም20 የመልካም ተግባር ወሮታው ክፉ ነውን? እነርሱ ግን ጕድጓድ ቈፈሩልኝ፤ ቍጣህን ከእነርሱ እንድትመልስ፣ በፊትህ ቆሜ፣ ስለ እነርሱ እንደ ተናገርሁ ዐስብ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ለነፍሴ ጉድጓድ ቈፍረዋልና በውኑ በመልካም ፋንታ ክፉ ይመለሳልን? ስለ እነርሱ በመልካም ለመናገር ቁጣህንም ከእነርሱ ለመመለስ በፊትህ እንደ ቆምሁ አስታውስ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ለሰውነቴ ጕድጓድን ቈፍረዋል፤ በውኑ በመልካም ፈንታ ክፉ ይመለሳልን? ስለ እነርሱ በመልካም እናገር ዘንድ፥ ቍጣህንም ከእነርሱ ትመልስ ዘንድ በፊትህ እንደ ቆምሁ አስብ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ለነፍሴ ጕድጓድ ቈፍረዋልና በውኑ በመልካም ፋንታ ክፉ ይመለሳልን? ስለ እነርሱ በመልካም እናገር ዘንድ ቍጣህንም ከእነርሱ እመልስ ዘንድ በፊትህ እንደ ቆምሁ አስብ። 参见章节 |