Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 7:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 “ያም ዘመን በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ በተከራየው ምላጭ በአሦር ንጉሠ ነገሥት የራሳችሁን የጢማችሁንና የሰውነታችሁን ሁሉ ጠጒር ይላጫል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 በዚያ ቀን፣ እግዚአብሔር ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ በተከራየው ምላጭ፣ ማለትም በአሦር ንጉሥ፣ የራስና የእግር ጠጕራችሁን እንዲሁም ጢማችሁን ይላጫል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 በዚያን ቀን፤ እግዚአብሔር ከወንዝ ማዶ በተከራየው ምላጭ፤ ማለትም በአሦር ንጉሥ፤ የራስና የእግር ጠጉራችሁን እንዲሁም ጢማችሁን ይላጫል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከወ​ንዙ ማዶ ባመ​ጣው ታላቅ ምላጭ በአ​ሦር ንጉሥ የራ​ሱ​ንና የእ​ግ​ሩን ጠጕር ይላ​ጨ​ዋል፤ ምላ​ጩም ጢሙን ደግሞ ይላ​ጫል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 በዚያም ቀን እግዚአብሔር ከወንዙ ማዶ በተከራየው ምላጭ በአሦር ንጉሥ የራሱንና የእግሩን ጠጕር ይላጨዋል፥ ምላጩም ጢሙን ደግሞ ይበላል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 7:20
17 交叉引用  

በዐመፅ ላይ ዐመፅ ጨምራችሁ እንደገና መቀጣት የምትፈልጉት ለምንድን ነው? ራሳችሁ ለሕመም፥ ልባችሁም ሁሉ ለድካም የተጋለጠ ሆኖአል።


መጥረቢያ እንጨት በሚቈርጥበት በባለቤቱ ላይ መነሣት ይችላልን? መጋዝስ በሚሰነጥቅበት ሰው ላይ መነሣት ይችላልን? እንዲሁም በትር በሚይዘው ሰው ላይ ኀይል አይኖረውም።


እግዚአብሔር የግብጽን ባሕረ ልሳን ያደርቃል፤ ማንም ሰው በእግሩ መሻገር እንዲችል የኤፍራጥስን ወንዝ በኀይለኛ ነፋስ መትቶ ወደ ትናንሽ ሰባት ጅረቶች ይከፋፍለዋል።


ሕዝቅያስ በይሁዳ በነገሠ በዐሥራ አራተኛው ዓመት፥ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ላይ አደጋ ጥሎ ያዛቸው።


አሁን እኔ የአሦርን ንጉሥ ከኀይለኛ ሠራዊቱ ጋር በእነርሱ ላይ አስነሣዋለሁ፤ የሠራዊቱም አመጣጥ የኤፍራጥስን ወንዝ ሞልቶ እንደሚያጥለቀልቅ ማዕበል ይሆናል።


ሕዝቡ ግን ወደ ቀጣቸው አምላክ አልተመለሱም፤ ወይም የሠራዊት አምላክን የሚሹ ሆነው አልተገኙም።


ወደ ግብጽ ወርደሽ ከዓባይ ወንዝ ውሃ መጠጣት የፈለግሽው ምን ጥቅም ለማግኘት ነው? ወደ አሦርስ ወርደሽ ከኤፍራጥስ ወንዝ ውሃ መጠጣት የፈለግሽው ምን የምታተርፊ መስሎሽ ነው?


“የሰው ልጅ ሆይ! የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በጢሮስ ላይ አደጋ ለመጣል ተነሥቶአል፤ ራሳቸው እስኪመለጥና ትከሻቸው እስኪቈስል ወታደሮቹን ከባድ ሸክም እንዲሸከሙ አድርጎአቸዋል፤ ይሁን እንጂ ንጉሡም ሆነ ሠራዊቱ በዚህ ሁሉ ድካማቸው ምንም ያተረፉት ነገር የለም።


የእርሱ ሠራዊት እኔን ስላገለገለ ግብጽን የድካሙ ዋጋ አድርጌ እሰጠዋለሁ። እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።’


跟着我们:

广告


广告