ኢሳይያስ 63:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ይመልሳል “እኔ ብቻዬን አሕዛብን ሁሉ እንደ ወይን ረገጥኩ፤ ይህን በማደርግበት ጊዜ ከሕዝቦች ከእኔ ጋር ማንም አልነበረም፤ እኔ በቊጣዬ ረገጥኳቸው፤ በመዓቴም አደቀቅኋቸው፤ ደማቸውም በልብሴ ላይ ተረጨ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም3 “እኔ በመጭመቂያው ወይኑን ብቻዬን ረገጥሁ፤ ከመንግሥታት ማንም ከእኔ ጋራ አልነበረም፤ በቍጣዬ ረገጥኋቸው፤ በመዓቴም ጨፈለቅኋቸው፤ ደማቸው በመጐናጸፊያዬ ላይ ተረጭቷል፤ ልብሴንም በክዬዋለሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 “መጥመቂያውን ብቻዬን ረግጫለሁ፥ ከአሕዛብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አልነበረም፤ በቁጣዬ ረገጥኋቸው በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፤ ደማቸውም በልብሴ ላይ ተረጭቶአል፥ ልብሴንም ሁሉ አሳድፌአለሁ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 መጭመቂያውን ብቻዬን ረግጫለሁ፤ ከአሕዛብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አልነበረም፤ በቍጣዬም ረገጥኋቸው፤ በመዓቴም ወደ መሬት ጣልጥህዋቸው፤ ደማቸውንም በምድር ላይ አፈሰስሁ፤ ልብሴም ሁሉ በደም ታለለ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 መጥመቂያውን ብቻዬን ረግጫለሁ፥ ከአሕዛብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አልነበረም፥ በቍጣዬ ረገጥኋቸው በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፥ ደማቸዋም በልብሴ ላይ ተረጭቶአል፥ ልብሴንም ሁሉ አሳድፌአለሁ። 参见章节 |