Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 62:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በቅጥር በሩ በኩል ዕለፉ፤ ለሰዎች መንገዱን አዘጋጁ፤ አውራ ጐዳናውን ሥሩ፤ ድንጋዮችን አስወግዱ፤ አርማውንም ለሕዝቦች ከፍ አድርጉ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ዕለፉ፤ በበሮቹ በኩል ዕለፉ፤ ለሕዝቡ መንገድ አዘጋጁ፤ አስተካክሉ፤ ጐዳናውን አስተካክሉ! ድንጋዩን አስወግዱ፤ ለመንግሥታትም ምልክት አሳዩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እለፉ፥ በበሮች በኩል እለፉ፤ የሕዝቡንም መንገድ ጥረጉ፤ አዘጋጁ፥ ጎዳናውን አዘጋጁ፥ ድንጋዮቹንም አስወግዱ፤ ለአሕዛብም ዓርማ አሳዩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ሂዱና በበሬ ውስጥ ግቡ፤ ለሕ​ዝ​ቤም መን​ገ​ድን ጥረጉ፤ ድን​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ከጎ​ዳ​ናው አስ​ወ​ግዱ፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም አላማ ያዙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እለፉ፥ በበሮች በኩል እለፉ፥ የሕዝቡንም መንገድ ጥረጉ፥ አዘጋጁ፥ ጎዳናውን አዘጋጁ፥ ድንጋዮቹንም አስወግዱ፥ ለአሕዛብም ዓላማ አነሡ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 62:10
27 交叉引用  

እናንተ በሮች ራሳችሁን ከፍ አድርጉ፤ የክብር ንጉሥ ይገባ ዘንድ እናንተ ጥንታውያን በሮች ተከፈቱ።


ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ለስሙም የምስጋና መዝሙር አቅርቡ፤ በደመናዎች ላይ ለሚጓዘው መንገድ አዘጋጁ፤ ስሙ እግዚአብሔር ነው፤ በፊቱ ደስ ይበላችሁ!


ሙሴም መሠዊያ ሠርቶ “እግዚአብሔር የድል ሰንደቅ ዓላማዬ ነው” ብሎ ሰየመው፤


በዚያን ጊዜ የእሴይ (የዳዊት) ዘር ለሕዝቦች ምልክት ሆኖ ይቆማል፤ ሕዝቦች እርሱን ይፈልጉታል፤ መኖሪያውም የተከበረ ይሆናል።


በዚያን ጊዜ ጌታ በመላው ዓለም ተበታትነው ይኖሩ የነበሩትን የእስራኤልንና የይሁዳን ሕዝብ ከአራቱ ማእዘን ሰብስቦ ያመጣቸው መሆኑን ለመንግሥታት ሁሉ የሚያሳውቅበትን አርማ ከፍ አድርጎ ያቆማል።


እግዚአብሔር የቀድሞ አባቶቻቸው ከግብጽ በወጡ ጊዜ እንዳደረገው ሁሉ አሁንም ከጥፋት የተረፉት የእስራኤል ሕዝብ ከአሦር የሚወጡበትን መንገድ ያዘጋጅላቸዋል።


በምድር የምትኖሩ ሁሉ አድምጡ! በተራሮች ጫፍ ላይ የተተከለ የሰንደቅ ዓላማ ምልክት ሲውለበለብ አስተውሉ! መለከት ሲነፋ ስሙ!


በዚያን ጊዜ በግብጽና በአሦር መካከል አውራ ጎዳና ይከፈታል፤ የእነዚህ ሁለት አገር ሕዝቦች አንዱ ወገን ወደ ሌላ ይተላለፋሉ፤ የሁለቱም ሕዝቦች አምልኮ አንድ ዐይነት ይሆናል።


በዚያን ጊዜ በይሁዳ ምድር የሚከተለው መዝሙር ይዘመራል፦ ጠንካራ ከተማ አለን፤ እንደ ቅጥርና እንደ ምሽግ የጸና መዳኛም አድርጎላታል።


እምነቱን የጠበቀ እውነተኛ ሕዝብ እንዲገባ የከተማይቱን በሮች ክፈቱ፤


በዚያ “ቅዱስ ጐዳና” የሚባል መንገድ ይኖራል፤ እርሱም ለእግዚአብሔር ሰዎች ይሆናል፤ ንጹሕ ያልሆነ ሰው በዚያ መንገድ አይሄድም፤ ሞኞችም ሊሄዱበት አይችሉም።


አንበሶችም ሆነ ነጣቂ አውሬዎች በዚያ አይገኙም፤ በዚያ መንገድ የሚመላለሱ እግዚአብሔር የታደጋቸው ወገኖች ብቻ ይሆናሉ።


እንዲህ የሚል ድምፅ ይሰማል፦ “በምድረ በዳ የእግዚአብሔርን መንገድ አዘጋጁ! በበረሓም ለአምላካችን ጥርጊያ ጐዳና አብጁ!


ጐድጓዳውና ሸለቆው ይሙላ፤ ተራራውና ኰረብታው ሁሉ ዝቅ ብሎ ይደልደል፤ ኮረብታውና ወጣ ገባ የሆነው ምድር ሁሉ ይስተካከል።


እንግዲህ ከባቢሎን ወጥታችሁ ሽሹ፤ “እግዚአብሔር አገልጋዩን እስራኤልን አድኖአል” የሚለውን የምሥራች ቃል በደስታ አብሥሩ፤ በየስፍራውም እንዲታወቅ አድርጉ።


“ተራሮቼን ደልድዬ መንገድ አደርጋለሁ፤ ጐዳናዎቼም ከፍ ይላሉ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ወንዶች ልጆችሽን በክንዳቸው፥ ሴቶች ልጆችሽንም በትከሻቸው ተሸክመው ያመጡ ዘንድ ለመንግሥታት ምልክት እሰጣለሁ፤ ለሕዝቦችም ዐርማን አነሣለሁ።


እናንተ የቤተ መቅደስን ንዋያተ ቅድሳት የተሸከማችሁ! ከባቢሎን ውጡ፤ ከእርሱም ተለዩ፤ ርኩስ የሆነውን ነገር አትንኩ፤ ከመካከልዋም ወጥታችሁ ራሳችሁን አንጹ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አስተካክሉ፥ አስተካክሉ፥ መንገዱን ጥረጉ! ሕዝቤ ከሚሄዱበት መንገድ መሰናክሉን አስወግዱ!”


የሕዝቦችን፥ ሀብትና ንጉሦቻቸውን ያመጡ ዘንድ በሮችሽ ሌሊትና ቀን ክፍት ይሆናሉ እንጂ አይዘጉም።


ከእንግዲህ ወዲህ በምድርሽ የዐመፅ ድምፅ በድንበሮችሽም ጥፋት ወይም ውድመት አይሰማም፤ ነገር ግን ቅጥሮችሽን መዳን የቅጥር በሮችሽን ምስጋና ብለሽ ትጠሪአቸዋለሽ።


በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፤ ከሞት ከተረፉት መካከል ስለ እኔ ወዳልሰሙትና ክብሬንም ወዳላዩት ወደ ተለያዩ ሕዝቦች ወደ ተርሴስ፥ ወደ ሊብያውያን ቀስት ወደሚያስፈነጥሩ ወደ ሊድያውያን፥ ወደ ቱባል፥ ወደ ግሪክ፥ ራቅ ብለው ወደሚገኙት ደሴቶችም እልካቸዋለሁ፤ እነርሱም በሕዝቦች መካከል ክብሬን ይገልጣሉ።


ሕዝቤ ግን እኔን ረስተዋል፤ ከንቱ ለሆኑ ጣዖቶችም ዕጣን ያጥናሉ፤ እነርሱም ባልታወቀ መንገድ እንዲሄዱ አድርገዋቸዋል፤ ተሰናክለውም የቀድሞውን መንገድ ትተዋል።


ለጽዮን መንገዱን አመልክቱአት! ሳትዘገዩ የደኅንነት ዋስትና ወደሚገኝበት ስፍራ ሽሹ! እግዚአብሔር ከሰሜን በኩል መቅሠፍትና ታላቅ ጥፋት ሊያመጣ ነው።


“የሰው ልጅ ሆይ! በጢሮስ ከተማ ያሉ ሕዝቦች የሚደሰቱበት ነገር ይህ ነው፦ ‘ኢየሩሳሌም ፈራርሳለች! የንግድ ኀይልዋም ወድቋል፤ ከእንግዲህ ወዲያ ከእኛ ጋር መወዳደር ከቶ ስለማትችል እኛ እንበለጽጋለን’ ይላሉ።


ስለዚህ በየአውራ ጐዳናው ሂዱና ያገኛችሁትን ሰው ሁሉ ወደ ሠርጉ ግብዣ ጥሩ።’


አንካሳ የሆነው እንዲፈወስ እንጂ ከቦታው ወጥቶ እንዳይናጋ ለእግራችሁ የቀና መንገድ አድርጉ።


跟着我们:

广告


广告