Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 54:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በአንቺ ላይ አደጋ ለማድረስ የተነሡ ቢኖሩ ከእኔ የተላኩ ስላልሆኑ ይወድቃሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ማንም ጕዳት ቢያደርስብሽ፣ ከእኔ አይደለም፤ ጕዳት ያደረሰብሽ ሁሉ ለአንቺ እጁን ይሰጣል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እነሆ፥ ጥቃት ቢደርስብሽ፥ ከእኔ ዘንድ ግን አይሆንም፤ በአንቺም ላይ የሚነሡ ሁሉ ከአንቺ የተነሣ ይወድቃሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እነሆ፥ መጻ​ተ​ኞች በእኔ ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ፤ በአ​ን​ቺም ይማ​ጸ​ናሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እነሆ፥ ይሰበሰባሉ፥ ነገር ግን ከእኔ ዘንድ አይሆንም፥ በአንቺም ላይ የሚሰበሰቡ ሁሉ ከአንቺ የተነሣ ይወድቃሉ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 54:15
16 交叉引用  

ተሰባስበው ይሸምቁብኛል፤ እርምጃዬን ሁሉ ይከታተላሉ፤ ሕይወቴንም ለማጥፋት ያደባሉ።


የባርነት ጊዜዋ እንዳለቀ፥ ለፈጸመችው ኃጢአት ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ እጥፍ ቅጣት እንደ ተቀበለችና ኃጢአትዋም ይቅር እንደ ተባለላት ለኢየሩሳሌም በለሰለሰ አነጋገር ንገሯት።”


አዳኛችሁ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ስለ እናንተ በባቢሎን ላይ የሚዘምት ሠራዊት እልካለሁ፤ የከተማዋን ቅጽር በሮች እሰባብራለሁ፤ የባቢሎናውያንም ፉከራ ወደ ለቅሶ ይለወጣል።


“እነሆ፥ በወናፉ ፍሙን የሚያናፋውን ብረት አቅላጭ የፈጠርኩ እኔ ነኝ፤ እርሱም መሣሪያውን የሚሠራው ለየተሠራለት ዓላማ እንዲውል ለማድረግ ነው፤ ያጠፋ ዘንድ አጥፊውን የፈጠርኩ እኔ ነኝ።


በዚያን ቀን ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ እንደ ከባድ ድንጋይ አደርጋታለሁ፤ እርስዋን ለማንሣት የሚሞክር ሁሉ ራሱን ይጐዳል፤ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ እርስዋን ለማጥቃት ተባብረው ይመጣሉ፤


በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም ላይ በጠላትነት የሚነሡትን የአሕዛብ መንግሥታት ሁሉ ለመደምሰስ እነሣለሁ።


እናንተን የሚነካ የእርሱን ዓይን ብሌን እንደሚነካ ሆኖ ይቈጠራል። የክብር ጌታ በበዘበዙአችሁ ሕዝቦች ላይ በላከኝ ጊዜ የተናገራቸው ቃላት እነዚህ ናቸው።


እነርሱ ተአምራት የሚያደርጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸው፤ እነዚህ መናፍስት ሁሉን በሚችል አምላክ ታላቅ ቀን ለሚሆነው ጦርነት ሰዎችን ለመሰብሰብ ወደ ዓለም ነገሥታት ሁሉ ይሄዳሉ።


跟着我们:

广告


广告