Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 52:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከማንኛውም ሰው በላይ መልኩ በጣም ተጐሳቊሎ ስለ ነበረ ሁናቴውን ያዩ ሰዎች አብዛኞቹ በጣም ደነገጡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ብዙዎች በርሱ እስኪደነግጡ ድረስ፣ መልኩ ከማንም ሰው ተለየ፤ ከሰው ልጆችም ሁሉ ይልቅ ተጐሳቈለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ፊቱ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ፥ መልኩም ከሰዎች ልጆች ይልቅ ተጐሳቁሎአልና ብዙ ሰዎች ስለ አንተ እንደ ተደነቁ፥ እንዲሁ ብዙ አሕዛብን ያስደንቃል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ፊቱ ከሰ​ዎች ሁሉ ይልቅ፥ መል​ኩም ከሰ​ዎች ልጆች ይልቅ ያለ ክብር ነውና ብዙ ሰዎች ስለ እርሱ ያደ​ን​ቃሉ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ፊቱ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ፥ መልኩም ከሰዎች ልጆች ይልቅ ተጐሳቍሎአልና ብዙ ሰዎች ስለ አንተ እንደ ተደነቁ፥ እንዲሁ ብዙ አሕዛብን ያስደንቃል፥

参见章节 复制




ኢሳይያስ 52:14
21 交叉引用  

ጒሮሮዬ እንደ ሸክላ ደረቀ፤ ምላሴም ከላንቃዬ ጋር ተጣበቀ፤ እንደ ሞተ ሰው በትቢያ ላይ ተውከኝ።


አጥንቶቼ ተቈጠሩ፤ ጠላቶቼም አተኲረው እያዩ በማፌዝ ተመለከቱኝ።


አንተ ብርቱ ተከላካይ ስለ ሆንክልኝ ሕይወቴ ለብዙዎች ምሳሌ ሆኖአል።


ለሚገርፉኝ ጀርባዬን፥ ጢሜንም ለሚነጩ ጒንጬን ሰጠኋቸው፤ ከሚሰድቡኝና ከሚተፉብኝ ፊቴን አላዞርኩም።


በዚያን ጊዜ ምራቃቸውን ተፉበት፤ ጎሸሙት፤ በጥፊም እየመቱት፥


ኢየሱስ ግን ገዢው እስኪደነቅ ድረስ ለአንዲት ክስ እንኳ ቃል አልመለሰለትም።


ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ተናግሮ ባበቃ ጊዜ ሕዝቡ በትምህርቱ ተደነቁ።


ደቀ መዛሙርቱም በጣም ተገረሙና፥ “ታዲያ በዚህ ሁኔታ ማን ሊድን ይችላል?” ተባባሉ።


ወደ ኢየሩሳሌም በሚወስደው መንገድ ሳሉ፥ ኢየሱስ እፊት እፊታቸው ይሄድ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱም በዚህ ነገር ተገረሙ፤ በስተኋላ የሚከተሉትም ፈርተው ነበር። እንደገናም ዐሥራ ሁለቱን ወደ እርሱ አቅርቦ፥ ስለሚደርስበት ነገር እንዲህ ሲል ገለጸላቸው፦


እርስዋ የዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ስለ ነበረች ወዲያውኑ ተነሥታ ወዲያና ወዲህ ማለት ጀመረች፤ ይህም በሆነ ጊዜ ሰዎቹ እጅግ ተደነቁ።


ወደ ጀልባውም ገብቶ፥ ከእነርሱ ጋር በሆነ ጊዜ ነፋሱ ቆመ፤ ደቀ መዛሙርቱ በጣም ተደነቁ።


የሰሙትም ሁሉ እጅግ በጣም በመደነቅ፦ “ሁሉን ነገር በመልካም አደረገ! ደንቆሮዎች እንዲሰሙ፥ ድዳዎች እንዲናገሩ ያደርጋል!” አሉ።


የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ይገረሙ ነበር።


ፊቱንም እየሸፈኑ፥ “ማን ነው የመታህ? ነቢይ ከሆንክ እስቲ ዕወቅ!” ይሉት ነበር።


ሁሉም በመደነቅ እርስ በርሳቸው፥ “ይህ ምን ዐይነት ቃል ነው? በሥልጣንና በኀይል ርኩሳን መናፍስትን ያዛል፤ እነርሱም ታዘው ይወጣሉ፤” ተባባሉ።


በዚያም የነበሩ ሰዎች ሁሉ እጅግ ተገርመው፥ በመፍራት፥ “ዛሬ ድንቅ ነገር አየን፤” እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።


跟着我们:

广告


广告