ኢሳይያስ 49:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ወንዶች ልጆችሽን በክንዳቸው፥ ሴቶች ልጆችሽንም በትከሻቸው ተሸክመው ያመጡ ዘንድ ለመንግሥታት ምልክት እሰጣለሁ፤ ለሕዝቦችም ዐርማን አነሣለሁ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ አሕዛብን በጥቅሻ እጣራለሁ፤ ዐርማዬንም ለሕዝቦች ከፍ አደርጋለሁ፤ ወንዶች ልጆችሽን በዕቅፋቸው ያመጡልሻል፤ ሴቶች ልጆችሽንም በትከሻቸው ይሸከሙልሻል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እጄን ወደ አሕዛብ አነሣለሁ፥ ዓላማዬንም ወደ ወገኖች አቆማለሁ፤ ወንዶች ልጆችሽንም በዕቅፋቸው ያመጡአቸዋል፥ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃቸው ላይ ይሸከሙአቸዋል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ እጄን ወደ አሕዛብ አነሣለሁ፤ ዓርማዬንም ወደ ደሴቶች አቆማለሁ፤ ወንዶች ልጆችሽንም በብብታቸው ታቅፈው ያመጡአቸዋል፤ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃቸው ላይ ይሸከሙአቸዋል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እጄን ወደ አሕዛብ አነሣለሁ፥ ዓላማዬንም ወደ ወገኖች አቆማለሁ፥ ወንዶች ልጆችሽንም በብብታቸው ያመጡአቸዋል፥ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃቸው ላይ ይሸከሙአቸዋል። 参见章节 |